ኤርምያስ 9:23-24
ኤርምያስ 9:23-24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፤ ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ ባለጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ያጋሩ
ኤርምያስ 9 ያንብቡኤርምያስ 9:23-24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበበኛ በጥበቡ አይታበይ፤ ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይኵራራ፤ የሚመካ ግን፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በማወቁና፣ በምድር ላይ ምሕረትን፣ ፍትሕንና ጽድቅን የማደርግ መሆኔን በመረዳቱ፣ በዚህ ይመካ፤ እኔ በእነዚህ ነገሮች፣ እደሰታለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።
ያጋሩ
ኤርምያስ 9 ያንብቡኤርምያስ 9:23-24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፥ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፥ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር።
ያጋሩ
ኤርምያስ 9 ያንብቡ