ኢዮብ 11:13-15 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ኢዮብ 11:13-15 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣ በእጅህ ያለውን ኀጢአት ብታርቅ፣ ክፋትም በድንኳንህ እንዳይኖር ብታደርግ፣ በዚያ ጊዜ ሳታፍር ቀና ትላለህ፤ ያለ ፍርሀት ጸንተህ ትቆማለህ፤
ያጋሩ
ኢዮብ 11 NASVኢዮብ 11:13-15 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
“ሆኖም፥ ልብህን የቀና ብታደርግ እጅህንም ዘርግተህ ወደ እግዚአብሔር ብትጸልይ፥ ኃጢአትን ከእጅህ ብታርቅ፥ ክፉ ነገርም በቤትህ እንዲገኝ ባታደርግ፥ በዚያን ጊዜ ቀና ብለህ ያለ ኀፍረት ሁሉን ነገር ታያለህ፤ ያለ ፍርሀትም ጸንተህ መቆም ትችላለህ።
ያጋሩ
ኢዮብ 11 አማ05ኢዮብ 11:13-15 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
አንተ ልብህን ንጹሕ ብታደርግ፥ እጆችህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥ በእጆችህ በደል ቢኖር ካንተ አርቀው፤ በልብህም ኀጢአት አይኑር፤ በዚያን ጊዜ ፊትህ በንጹሕ ውኃ እንደ ታጠበ ያበራል፥ መተዳደፍህንም ታስወግዳለህ፥ አትፈራምም።
ኢዮብ 11:13-15 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥ አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥ በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፥ ትበረታለህ፥ አትፈራምም።
ያጋሩ
ኢዮብ 11 አማ54ኢዮብ 11:13-15 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
“አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጆችህን ወደ እርሱ ትዘረጋለህ፥ በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥ በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፥ ትበረታለህ፥ አትፈራምም።
ያጋሩ
ኢዮብ 11 መቅካእኤ