ኢዮብ 15:15-16 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ኢዮብ 15:15-16 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
እነሆ፤ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ ሰማያትም በርሱ ፊት ንጹሓን አይደሉም። ታዲያ፣ ክፋትን እንደ ውሃ የሚጠጣ፣ አስጸያፊና ርኩስ ሰውማ እንዴት ይታመን!
ያጋሩ
ኢዮብ 15 NASVኢዮብ 15:15-16 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
እግዚአብሔር በመላእክቱ ላይ እምነት የለውም፤ ሰማያት እንኳ በእርሱ ፊት ንጹሓን አይደሉም፤ የተበላሸና የረከሰ ኃጢአትንም እንደ ውሃ የሚጠጣ ሰውማ ምንኛ የባሰ ነው?
ያጋሩ
ኢዮብ 15 አማ05ኢዮብ 15:15-16 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
እነሆ፥ በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ ሰማይም በፊቱ ንጹሕ አይደለም። ይልቁንስ አስጸያፊና የረከሰ፥ ኀጢአትንም እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?
ኢዮብ 15:15-16 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
እነሆ፥ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም፥ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። ይልቁንስ አስጸያፊና የረከሰ፥ ኃጢአትንም እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?
ያጋሩ
ኢዮብ 15 አማ54ኢዮብ 15:15-16 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
እነሆ፥ ቅዱሳኑን እንኳን አያምናቸውም፥ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። ታዲያ አስጸያፊና የረከሰ፥ በደልን እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?!”
ያጋሩ
ኢዮብ 15 መቅካእኤ