ኢዮብ 17:11-12 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ኢዮብ 17:11-12 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ዕድሜዬ ዐለቀ፤ ዕቅዴም ከሸፈ፤ የልቤም ሐሳብ ከንቱ ሆነ። እነዚህ ሰዎች ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ ጨልሞም እያዩ፣ ‘ብርሃን ቀርቧል’ ይላሉ።
ያጋሩ
ኢዮብ 17 NASVኢዮብ 17:11-12 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
“የዕድሜዬ ዘመን ተፈጽሞአል፤ ዕቅዴና የልቤ ምኞት ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል። እነዚህ ሰዎች ሌሊቱን ቀን ነው ይላሉ፤ ብርሃኑን ደግሞ ሊጨልም ነው ይላሉ።
ያጋሩ
ኢዮብ 17 አማ05ኢዮብ 17:11-12 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
“ዘመኖች በጩኸት አለቁ፤ የልቤ ሥርም ተቈረጠ። ቀኑ ሌሊት ሆነብኝ። ከጨለማውም የተነሣ ብርሃኑ አጭር ነው።
ኢዮብ 17:11-12 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ዕድሜዬ አለፈች፥ አሳቤና የልቤ መሣርያ ተቈረጠ። ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፥ ብርሃኑም ወደ ጨለማ የቀረበ ይመስላቸዋል።
ያጋሩ
ኢዮብ 17 አማ54ኢዮብ 17:11-12 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ቀኖቼ አለፉ፥ ዕቅዴና የልቤ ምኞት ቀለጠ። ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፥ ብርሃኑም ወደ ጨለማ የቀረበ ይመስላቸዋል።
ያጋሩ
ኢዮብ 17 መቅካእኤ