ኢዮብ 20:4-5 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 20:4-5 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ ጊዜ ጀምሮ፣ ከጥንቱ እንዴት እንደ ነበረ ታውቃለህን? የኀጢአተኞች መፈንጨት ለዐጭር ጊዜ፣ የክፉዎችም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?

ኢዮብ 20:4-5 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“ሰው በምድር ላይ ከተገኘበት ጊዜ ጀምሮ ከጥንት እንደዚህ እንደ ሆነ ታውቃለህ። የክፉ ሰው ድንፋታ ለአጭር ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔርንም የሚክዱ ሰዎች ደስታቸው በቅጽበት የሚጠፋ ነው።

ኢዮብ 20:4-5 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሰው በም​ድር ላይ ከተ​ፈ​ጠረ፥ ከድሮ ዘመን ጀምሮ፥ በአ​ን​ተስ ዘመን እን​ደ​ዚህ ያለ ነገር ታው​ቃ​ለ​ህን? የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።

ኢዮብ 20:4-5 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ፥ ከዱሮ ዘመን ጀምሮ፥ የኃጢአተኛ ፉከራ አጭር መሆኑን የዝንጉዎችም ደስታ ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን?

ኢዮብ 20:4-5 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ፥ ከዱሮ ዘመን ጀምሮ፥ የክፉ ሰዎች ፉከራ አጭር መሆኑን አምላክን የሚክዱ ደስታቸው ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን?