ኢዮብ 22:21-22 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 22:21-22 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“ለእግዚአብሔር ተገዛ፤ ከርሱም ጋራ ሰላም ይኑርህ፤ በረከትም ታገኛለህ። ምክርን ከአፉ ተቀበል፤ ቃሉንም በልብህ አኑር።

ኢዮብ 22:21-22 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“ስለዚህ ኢዮብ ሆይ፥ ራስህን ለእግዚአብሔር አስገዛ፤ ከእርሱም ጋር ሰላም ይኑርህ፤ ይህን ብታደርግ መልካም ነገርን ታገኛለህ። እግዚአብሔር የሚሰጥህን ትምህርት ተቀበል፤ ቃሉንም በልብህ አኑር።

ኢዮብ 22:21-22 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“አሁ​ንም መታ​ገሥ ትችል እንደ ሆነ፥ ፍሬ​ህም ይበጅ እንደ ሆነ እስኪ ጽኑ ሁን። ከአ​ፉም ሕጉን ተቀ​በል፥ በል​ብ​ህም ቃሉን አኑር፤

ኢዮብ 22:21-22 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፥ በዚያም በጎነት ታገኛለህ። ከአፉም ሕጉን ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፥

ኢዮብ 22:21-22 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“እንግዲህ አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፥ በዚያም መልካምን ታገኛለህ። ከአፉም ትምህርቱን ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፥