ኢዮብ 23:12 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 23:12 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከአፉ ከወጣው ትእዛዝ አልራቅሁም፣ የአንደበቱን ቃል ከዕለት እንጀራዬ አብልጬ ይዣለሁ።

ኢዮብ 23:12 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከእርሱ ትእዛዞች አልወጣሁም፤ ቃሉንም በልቤ ውስጥ ጠብቄአለሁ።

ኢዮብ 23:12 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ከት​እ​ዛ​ዙም አላ​ለ​ፍ​ሁም፤ ቃሉን በልቤ ሰው​ሬ​አ​ለሁ።

ኢዮብ 23:12 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ከከንፈሩ ትእዛዝ አልተመለስሁም፥ የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ።

ኢዮብ 23:12 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከተናገራቸው ትእዛዛት አልኮበለልኩም፥ የአፉን ቃል በልቤ ደብቄአለሁ።