ኢዮብ 24:22-24 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ኢዮብ 24:22-24 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ነገር ግን እግዚአብሔር ኀያላንን በኀይሉ ጐትቶ ይጥላል፤ ቢደላደሉም የሕይወት ዋስትና የላቸውም። ያለ ሥጋት እንዲኖሩ ትቷቸው ይሆናል፤ ዐይኖቹ ግን በመንገዳቸው ላይ ናቸው። ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ሆኖም ይጠፋሉ፤ ዝቅ ዝቅ ብለው፤ እንደ ሌሎቹ ይከማቻሉ። እንደ እህል ራስም ይታጨዳሉ።
ኢዮብ 24:22-24 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ነገር ግን እግዚአብሔር በኀይሉ በሥልጣን ላይ ያሉትን ሰዎች ያስወግዳቸዋል። ኑሮአቸው የተሳካ ቢመስልም እንኳ የመኖር ዋስትና የላቸውም። እግዚአብሔር በሰላም እንዲኖሩ ቢፈቅድላቸውም እንኳ የሚሄዱበትን መንገድ ሁሉ አተኲሮ ይመለከታል። ክፉ ሰዎች ለጥቂት ጊዜ ይበለጽጋሉ፤ ነገር ግን ወዲያውኑ እንደ አረም ጠውልገው ይጠፋሉ፤ እንደ እህልም ይታጨዳሉ።
ኢዮብ 24:22-24 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ነገር ግን ረዳት የሌላቸውን በቍጣው አጠፋቸው። እርሱም በተነሣ ጊዜ ሰው በሕይወቱ አይታመንም። በታመመም ጊዜ መዳንን ተስፋ አያደርግም። ነገር ግን እርሱ በሕማሙ ይሞታል። ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙዎችን አስጨነቃቸው። እንደ አመድማዶ በሙቀት ይጠወልጋል። ከቃርሚያው እንደሚወድቅ እሸትም ይቈረጣል።
ኢዮብ 24:22-24 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ነገር ግን በኃይሉ ኃያላንን ይስባል፥ እርሱም በተነሣ ጊዜ ሰው በሕይወቱ አይታመንም። እግዚአብሔር በደኅና አኑሮአቸዋል፥ በዚያም ይታመናሉ፥ ዓይኖቹ ግን በመንገዳቸው ላይ ናቸው። ጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፥ ይሄዳሉ፥ ይጠወልጋሉም፥ እንደ ሌሎች ሁሉ ይከማቻሉ፥ እንደ እሸትም ራስ ይቈረጣሉ።
ኢዮብ 24:22-24 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ነገር ግን በኃይሉ ኃያላንን ያስቀጥላል፥ እርሱም በተነሣ ጊዜ ሰው በሕይወቱ አይታመንም። እግዚአብሔር በደኅና አኑሮአቸዋል፥ በዚያም ይታመናሉ፥ ዐይኖቹ ግን መንገዳቸውን ይመለከታሉ። ጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፥ ይሄዳሉ፥ ይጠወልጋሉም፥ እንደ ሌሎች ሁሉ ይከማቻሉ፥ እንደ እሸትም ራስ ይቈረጣሉ።