ኢዮብ 25:5-6 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 25:5-6 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በፊቱ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፣ ከዋክብትም ንጹሓን ካልሆኑ፣ ይልቁን ከብል የሚቈጠር የሰው ልጅ፣ ትል የሆነውማ ሰው ምንኛ ያንስ!”

ኢዮብ 25:5-6 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጨረቃ እንኳ ደማቅ አይደለችም፤ ከዋክብትም በእርሱ ፊት ንጹሖች አይደሉም። በስባሽና ትል የሆነው ሟች ሰውማ ምንኛ የባሰ ነው?”

ኢዮብ 25:5-6 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ይሰ​ወ​ራል፤ አያ​በ​ራ​ምም፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም በፊቱ ንጹ​ሓን አይ​ደ​ሉም። ይል​ቁ​ንስ ፈራሽ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!”

ኢዮብ 25:5-6 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!

ኢዮብ 25:5-6 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን ካልሆኑ። ይልቁንስ ፈራሽ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!”