ኢዮብ 26:7 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 26:7 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋው፤ ምድርንም እንዲያው በባዶው ላይ አንጠለጠላት።

ኢዮብ 26:7 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እግዚአብሔር የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋ፤ ምድርም በባዶ ቦታ እንድትንጠለጠል አደረገ።

ኢዮብ 26:7 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሰማ​ይን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘ​ረ​ጋል፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አን​ዳች አልባ ያን​ጠ​ለ​ጥ​ላል።

ኢዮብ 26:7 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም በታችዋ አንዳች አልባ ያንጠለጥላል።

ኢዮብ 26:7 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም ያለአንዳች ድጋፍ ያንጠለጥላል።