ኢዮብ 28:12-13 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 28:12-13 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“ነገር ግን ጥበብ ከወዴት ትገኛለች? ማስተዋልስ መኖሪያዋ የት ነው? ሰው ዋጋዋን አያውቅም፤ በሕያዋንም ምድር አትገኝም።

ኢዮብ 28:12-13 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ታዲያ፥ ጥበብ ከየት ትገኛለች? ማስተዋልስ ቦታዋ የት ነው? “ጥበብ ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶች በሚኖሩባት ምድር አትገኝም፤ እውነተኛ ዋጋዋንም የሚያውቅ ሰው የለም።

ኢዮብ 28:12-13 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“ነገር ግን ጥበብ ወዴት ትገ​ኛ​ለች? የጥ​በ​ብስ ሀገ​ርዋ ወዴት ነው? ሟች ሰው መን​ገ​ድ​ዋን አያ​ው​ቅም፤ በሰ​ዎ​ችም ዘንድ አት​ገ​ኝም።

ኢዮብ 28:12-13 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ነገር ግን ጥበብ የምትገኘው ወዴት ነው? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው? ሰው መንገድዋን አያውቅም፥ በሕያዋን ምድር አትገኝም።

ኢዮብ 28:12-13 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“ነገር ግን ጥበብ የምትገኘው ወዴት ነው? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው? ሰው መንገድዋን አያውቅም፥ በሕያዋን አገር አትገኝም።