ኢዮብ 30:20 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 30:20 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“አምላክ ሆይ፤ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ነገር ግን አልመለስህልኝም፤ በፊትህም ቆምሁ፤ አንተ ግን ዝም አልኸኝ።

ኢዮብ 30:20 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ለመንኩ፤ ነገር ግን አልመለስክልኝም፤ ቆሜም ወደ አንተ ጸለይኩ፤ አንተ ግን ፊትህን አልመለስክልኝም።

ኢዮብ 30:20 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አል​ሰ​ማ​ኸ​ኝ​ምም፤ እነ​ርሱ ግን ቆመው ተመ​ለ​ከ​ቱኝ።

ኢዮብ 30:20 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልመለስህልኝም፥ ተነሣሁ፥ አልተመለከትኸኝም።

ኢዮብ 30:20 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልመለስህልኝም፥ ተነሣሁ፥ ነገር ግን ዝም ብለህ ተመለከትኸኝ።