ኢዮብ 34:10-11 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 34:10-11 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“ስለዚህ፣ እናንተ አስተዋዮች ስሙኝ፤ ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ፣ በደልንም መፈጸም ሁሉን ቻይ አምላክ ይራቅ። ለሰው እንደ ሥራው ይመልስለታል፤ እንደ አካሄዱም ይከፍለዋል።

ኢዮብ 34:10-11 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“አስተዋዮች የሆናችሁ ሰዎች አድምጡኝ! ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር፥ ስሕተትንም ማድረግ ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ! እግዚአብሔር ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፤ በአካሄዱም መጠን የሚገባውን ያደርግለታል።

ኢዮብ 34:10-11 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“ሰለ​ዚህ እና​ንተ አእ​ምሮ ያላ​ቸሁ ሰዎች ስሙኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ትበ​ድሉ ዘንድ አት​ው​ደዱ። ሁሉን በሚ​ችል አም​ላክ ፊትም ጻድ​ቁን አታ​ው​ኩት። ለሰው ሁሉ እንደ ሥራው ይመ​ል​ስ​ለ​ታል፥ ሰው​ንም እንደ መን​ገዱ ያገ​ኘ​ዋል።

ኢዮብ 34:10-11 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ስለዚህ እናንተ አእምሮ ያላችሁ ሰዎች፥ ስሙኝ፥ ክፋትን ያደርግ ዘንድ ከእግዚአብሔር፥ በደልንም ይሠራ ዘንድ ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ። ለሰው ሥራውን ይመልስለታል፥ ሰውም እንደ መንገዱ ያገኝ ዘንድ ያደርጋል።

ኢዮብ 34:10-11 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“ስለዚህ የምታስተውሉ ሰዎች፥ ስሙኝ፥ ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር፥ በደልንም መፈጸም ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ። ለሰው እንደ ሥራው ይመልስለታል፥ ሰውም እንደ መንገዱ ያገኝ ዘንድ ያደርጋል።