ኢዮብ 5:8-9 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 5:8-9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“እኔ ብሆን ኖሮ፣ ወደ እግዚአብሔር በቀረብሁ፣ ጕዳዬንም በፊቱ በገለጽሁለት ነበር። እርሱ፣ የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮች፣ የማይቈጠሩም ታምራት ያደርጋል።

ኢዮብ 5:8-9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ወደ እግዚአብሔር እማጠን ነበር፤ ችግሬን ሁሉ እገልጥለት ነበር። እርሱ የማይቈጠረውን ተአምራት፦ የማይመረመረውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።

ኢዮብ 5:8-9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እለ​ም​ነው ነበር፥ የሁሉ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጠ​ራው ነበር። እርሱ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን ታላቅ ነገ​ርና የማ​ይ​ቈ​ጠ​ረ​ውን የከ​በ​ረና ድንቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።

ኢዮብ 5:8-9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምን ነበር፥ ነገሬንም ወደ እግዚአብሔር አቀርብ ነበር። የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን ተአምራት ያደርጋል።

ኢዮብ 5:8-9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምን ነበር፥ ነገሬንም ወደ እግዚአብሔር አቀርብ ነበር። የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን ተአምራት ያደርጋል።