ኢዮብ 7:17-18 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 7:17-18 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“ከፍ ከፍ ታደርገው ዘንድ፣ ልብህንም ትጥልበት ዘንድ ሰው ምንድን ነው? በየማለዳው ትመረምረዋለህ፤ በየጊዜውም ትፈትነዋለህ።

ኢዮብ 7:17-18 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“ግምት ትሰጠው ዘንድና ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? በየማለዳውስ ትመረምረው ዘንድ በየጊዜውስ ትፈትነው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?

ኢዮብ 7:17-18 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሰው ምን​ድን ነው? ከፍ ከፍ ታደ​ር​ገው ዘንድ፥ ልቡ​ና​ው​ንም ትጐ​በ​ኘው ዘንድ፥ ማለዳ ማለ​ዳስ ትጐ​በ​ኘው ዘንድ፥ በዕ​ረ​ፍ​ቱም ትፈ​ር​ድ​ለት ዘንድ፥

ኢዮብ 7:17-18 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ሰው ምንድር ነው ታከብረው ዘንድ፥ ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ፥ ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥ ሁልጊዜስ ትፈታተነው ዘንድ?

ኢዮብ 7:17-18 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ሰው ምንድነው ታከብረው ዘንድ፥ ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ፥ ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥ ሁልጊዜስ ትፈታተነው ዘንድ?