ኢዮብ 8:20-21 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 8:20-21 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“እነሆ፤ እግዚአብሔር እንከን የሌለበትን ሰው አይጥልም፤ የክፉዎችንም እጅ አያበረታም፤ እንደ ገና አፍህን በሣቅ፣ ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላል።

ኢዮብ 8:20-21 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን አይጥላቸውም፤ ክፉዎችንም አይረዳቸውም። ስለዚህ አንተንም በደስታ እንድትስቅና ‘እልል’ እንድትል ያደርግሃል።

ኢዮብ 8:20-21 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዋ​ሁን ሰው አይ​ጥ​ለ​ውም፥ የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞ​ች​ንም እጅ አያ​በ​ረ​ታም። የዝ​ን​ጉ​ዎ​ች​ንም መባ አይ​ቀ​በ​ልም። የቅ​ኖ​ችን አፍ ሳቅ ይሞ​ላል፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስ​ጋና ይሞ​ላል።

ኢዮብ 8:20-21 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እነሆ፥ እግዚአብሔር ፍጹሙን ሰው አይጥለውም፥ የኃጢአተኞችንም እጅ አያበረታም። አፍህን እንደ ገና ሳቅ ይሞላል፥ ከንፈሮችህንም እልልታ ይሞላል።

ኢዮብ 8:20-21 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“እነሆ፥ እግዚአብሔር ፍጹሙን ሰው አይጥለውም፥ የክፉዎችን እጅ አያበረታም። አፍህን እንደገና በሳቅ፥ ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላዋል።