ኢዮብ 8:5-7 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 8:5-7 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ነገር ግን አንተ ወደ እግዚአብሔር ብትመለከት፣ ሁሉን ቻይ አምላክን ብትማፀን፣ ንጹሕና ጻድቅ ብትሆን፣ እርሱ ስለ አንተ አሁኑኑ ይነሣል፤ ወደ ተገቢውም ስፍራህ ይመልስሃል። ጅማሬህ አነስተኛ ቢመስልም፣ ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።

ኢዮብ 8:5-7 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ብትመለስ፥ ሁሉን ቻዩን አምላክ ብትለምነው፥ ቀጥተኛና ንጹሕ ከሆንክ፥ እርሱ ፈጥኖ ወደ ተገቢ ቦታህ ይመልስሃል። አጀማመርህ አነስተኛ መስሎ ቢታይም፥ የወደፊት ኑሮህ የተትረፈረፈ ይሆናል።

ኢዮብ 8:5-7 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“አንተ ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገሥ​ግሥ፥ ሁሉን ወደ​ሚ​ች​ለው አም​ላ​ክም ጸልይ፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ ብት​ሆን፥ ልመ​ና​ህን ፈጥኖ ይሰ​ማ​ሃል፥ የጽ​ድ​ቅ​ህ​ንም ብድ​ራት ፈጽሞ ይሰ​ጥ​ሃል። ጅማ​ሬ​ህም ታናሽ ቢሆ​ንም እንኳ ፍጻ​ሜህ ቍጥር አይ​ኖ​ረ​ውም።

ኢዮብ 8:5-7 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እግዚአብሔርን ብትገሠግሥ፥ ሁሉንም የሚችለውን አምላክ ብትለምን፥ ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት አሁን ስለ አንተ ይነቃል፥ የጽድቅህንም መኖሪያ ያከናውንልሃል። ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ይበዛል።

ኢዮብ 8:5-7 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እግዚአብሔርን ብትሻ፥ ሁሉንም የሚችለውን አምላክ ብትማጸን፥ ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት እርሱ አንተን ነቅቶ ይጠብቅሃል፥ የጽድቅህንም መኖሪያ ያረጋግጥልሃል። ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ይበዛል።”