ዘሌዋውያን 11:44 - Compare All Versions
ዘሌዋውያን 11:44 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና፤ ሰውነታችሁን ቀድሱ፤ ቅዱሳንም ሁኑ፤ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና፤
ዘሌዋውያን 11:44 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ተለዩ፤ ቅዱሳንም ሁኑ፤ ምድር ለምድር በሚንቀሳቀስ በማንኛውም ፍጡር ራሳችሁን አታርክሱ።
ዘሌዋውያን 11:44 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና፤ ሰውነታችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤ በምድርም ላይ በሚሳብ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ሰውነታችሁን አታርክሱ።
ዘሌዋውያን 11:44 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ራሳችሁን የተቀደሰ አድርጉ፤ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ነፍሳት በመብላት ራሳችሁን አታርክሱ።
ዘሌዋውያን 11:44 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና፤ ስለዚህ ራሳችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤ በምድርም ላይ በደረታቸው እየተሳቡ በሚርመሰመሱ ሁሉ የገዛ አካላችሁን አታርክሱ።