ዘሌዋውያን 23:3 - Compare All Versions

ዘሌዋውያን 23:3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ግን የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ጉባኤ ይሆ​ን​በ​ታል፤ ምንም ሥራ አት​ሠ​ሩም፤ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በት ነው።

ዘሌዋውያን 23:3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“ ‘ሥራ የምትሠሩበት ስድስት ቀን አላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው። የእግዚአብሔር ሰንበት ስለ ሆነ፣ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ምንም ዐይነት ሥራ አትሥሩበት።

ዘሌዋውያን 23:3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው፤ የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንበታል፤ ምንም ሥራ አትሠሩም፤ በምትኖሩበት ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው።

ዘሌዋውያን 23:3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሥራ የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ዕለተ ሰንበት ግን የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ለአምልኮ ተሰብሰቡ እንጂ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ሰንበት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕለት ነው፤

ዘሌዋውያን 23:3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው፤ የተቀደሰ ጉባኤ ይደረግበታል፤ ምንም ሥራ አትሠሩም፤ በምትኖሩበት ሁሉ ለጌታ ሰንበት ነው።