ዘሌዋውያን 6:14 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ዘሌዋውያን 6:14 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“ ‘የእህል ቍርባን ሥርዐት ይህ ነው፦ የአሮን ልጆች ቍርባኑን በመሠዊያው ትይዩ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርቡት።
ዘሌዋውያን 6:14 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
“ስለ እህል መባ አቀራረብ የተደነገጉት መመሪያዎች እነዚህ ናቸው፦ ትውልዱ ከአሮን ዘር የሆነ ካህን የእህሉን መባ በመሠዊያው ፊት ለፊት ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤
ዘሌዋውያን 6:14 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
“የአሮን ልጆች በእግዚአብሔር ፊት በመሠዊያው ፊት ለፊት የሚያቀርቡት የመሥዋዕት ሥርዐት ይህ ነው።
ዘሌዋውያን 6:14 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
የእህሉም ቍርባን ሕግ ይህ ነው፤ የአሮን ልጆች በእግዚአብሔር ፊት በመሠዊያው ፊት ያቀርቡታል።
ዘሌዋውያን 6:14 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
“የእህሉም ቁርባን ሕግ ይህ ነው፤ የአሮን ልጆች በመሠዊያው ፊት ለፊት በጌታ ፊት ያቀርቡታል።