ሉቃስ 20:46-47
ሉቃስ 20:46-47 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“ልብሳቸውን አንዘርፍፈው ወዲያ ወዲህ ማለትን ከሚሹ፥ በገበያ እጅ መነሣትንና በአደባባይ ፊት ለፊት፥ በማዕድም ጊዜ በከበሬታ መቀመጫ መቀመጥን ከሚወዱ ጻፎች ተጠበቁ። የመበለቶችን ገንዘብ የሚበሉ፥ ለምክንያት ጸሎትንም የሚያስረዝሙ እነዚህ ታላቅ ፍርድን ይቀበላሉ።”
ያጋሩ
ሉቃስ 20 ያንብቡሉቃስ 20:46-47 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤ “ዘርፋፋ ቀሚስ ለብሰው መዞርን፣ በገበያ ስፍራ የአክብሮት ሰላምታን፣ በምኵራብ የከበሬታ መቀመጫን፣ በግብዣ ቦታም የክብር ስፍራን ይፈልጋሉና፤ በረዥም ጸሎታቸው እያሳበቡ የመበለቶችን ቤት ያራቍታሉ፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”
ያጋሩ
ሉቃስ 20 ያንብቡሉቃስ 20:46-47 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ፥ በገበያም ሰላምታ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤ የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ፥ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ አለ።
ያጋሩ
ሉቃስ 20 ያንብቡ