ሉቃስ 5:4-11

ሉቃስ 5:4-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ከፈ​ጸመ በኋላ ስም​ዖ​ንን፥ “ወደ ጥልቁ ባሕር ፈቀቅ በል፤ መረ​ቦ​ቻ​ች​ሁ​ንም ለማ​ጥ​መድ ጣሉ” አለው። ስም​ዖ​ንም መልሶ፥ “መም​ህር፥ ሌሊ​ቱን ሁሉ ደክ​መ​ናል፤ የያ​ዝ​ነ​ውም የለም፤ ነገር ግን ስለ አዘ​ዝ​ኸን መረ​ቦ​ቻ​ች​ንን እን​ጥ​ላ​ለን” አለው። እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸ​ውም ባደ​ረጉ ጊዜ፥ መረቡ እስ​ኪ​ቀ​ደድ ድረስ ብዙ ዓሣ ተያዘ። መጥ​ተ​ውም ይረ​ዱ​አ​ቸው ዘንድ በሌላ ታንኳ የነ​በ​ሩ​ትን ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠሩ፤ መጥ​ተ​ውም እስ​ኪ​ጠ​ልቁ ድረስ ሁለ​ቱን ታን​ኳ​ዎች ሞሉ። ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው። እር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሁሉ ስለ ተያ​ዘው ዓሣ ተደ​ን​ቀው ነበ​ርና። እን​ዲ​ሁም የስ​ም​ዖን ባል​ን​ጀ​ራ​ዎች የነ​በሩ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆች ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ንስ ተደ​ነቁ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ስም​ዖ​ንን፥ “አት​ፍራ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ሰውን ታጠ​ም​ዳ​ለህ” አለው። ታን​ኳ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር አወ​ጡና ሁሉን ትተው ተከ​ተ​ሉት።

ሉቃስ 5:4-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ስምዖንን፣ “ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ በልና ዓሣ ለመያዝ መረባችሁን ጣሉ” አለው። ስምዖንም መልሶ፣ “መምህር ሆይ፤ ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም ዐድረን ምንም አልያዝንም፤ አንተ ካልህ ግን መረቦቹን እጥላለሁ” አለው። እንደዚያም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረባቸውም ይበጣጠስ ጀመር። በሌላ ጀልባ የነበሩት ባልንጀሮቻቸው መጥተው እንዲያግዟቸውም በምልክት ጠሯቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱን ጀልባዎች በዓሣ ሞሏቸው፣ ጀልባዎቹም መስመጥ ጀመሩ። ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ፣ “ጌታ ሆይ፤ እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከእኔ ተለይ” አለው። ይህን ያለው እርሱና ከርሱ ጋራ የነበሩት በያዙት ዓሣ ብዛት ስለ ተደነቁ ነው፤ ደግሞም የስምዖን ባልንጀሮች የነበሩት የዘብዴዎስ ልጆች፣ ያዕቆብና ዮሐንስም ተደነቁ። ኢየሱስም ስምዖንን፣ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ” አለው። እነርሱም ጀልባዎቹን ወደ ምድር ካስጠጉ በኋላ፣ ሁሉን ትተው ተከተሉት።

ሉቃስ 5:4-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ንግግሩንም ከጨረሰ በኋላ ስምዖንን፦ “ጀልባዋን ወደ ጥልቁ ባሕር ራቅ አድርገህ አንተና ጓደኞችህ ዓሣ ለማጥመድ መረባችሁን ጣሉ፤” አለው። ስምዖንም “መምህር ሆይ! ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም አድረን ምንም አልያዝንም፤ አንተ ካልክ ግን፥ እነሆ! መረቡን እንጥላለን፤” አለው። መረቡን በጣሉ ጊዜ መረቡ እስኪቀደድ ድረስ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ። ስለዚህ በሌላይቱ ጀልባ ላይ የነበሩት ጓደኞቻቸው መጥተው እንዲያግዙአቸው በጥቅሻ ጠሩአቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱ ጀልባዎች ሊሰምጡ ጥቂት እስኪቀራቸው ድረስ በዓሣ ሞሉአቸው። ስምዖን ጴጥሮስ ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ፊት ተንበርክኮ፥ “ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ስለ ሆንኩ ወደ እኔ አትቅረብ!” አለው። ይህንንም ያለበት ምክንያት እርሱና አብረውት የነበሩት ጓደኞቹ ሁሉ ከያዙት ዓሣ ብዛት የተነሣ እጅግ ተገርመው ስለ ነበር ነው። እንዲሁም የስምዖን ጓደኞች የሆኑት የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተገርመው ነበር። ኢየሱስ ስምዖንን፦ “አይዞህ አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰዎችን የምታጠምድ ትሆናለህ፤” አለው። እነርሱም ጀልባዎቹን ወደ ምድር ካስጠጉ በኋላ ሁሉን ነገር ትተው የኢየሱስ ተከታዮች ሆኑ።

ሉቃስ 5:4-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ንግግሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ “ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል፤ መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ፤” አለው። ስምዖንም መልሶ፦ “አቤቱ! ሌሊቱን ሙሉ ብንደክምም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ፤” አለው። ይህንም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረቦቻቸውም ተቀደዱ። በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው በምልክት ጠሩአቸው፤ መጥተውም ሁለቱን ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው። ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ፊት ወድቆ፦ “ጌታ ሆይ! እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከኔ ራቅ፤” አለው። እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ስላጠመዱት ዓሣ ተደንቀው ነበርና፤ እንዲሁም ደግሞ የስምዖን ወዳጆች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተደነቁ። ኢየሱስም ስምዖንን፦ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰዎችን የምታጠምድ ትሆናለህ፤” አለው። ታንኳዎቹንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።