ማቴዎስ 14:3-5
ማቴዎስ 14:3-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ቀደም ሲል ሄሮድስ፣ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ ወህኒ አስገብቶት ነበር። ምክንያቱም ዮሐንስ፣ “እርሷን እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም” ይለው ነበር። ሄሮድስም ዮሐንስን ሊገድለው ፈልጎ ነበር፤ ሕዝቡ ግን እንደ ነቢይ ይመለከተው ስለ ነበር ፈራ።
Share
ማቴዎስ 14 ያንብቡማቴዎስ 14:3-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤ ዮሐንስ “እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም፤” ይለው ነበርና። ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው።
Share
ማቴዎስ 14 ያንብቡማቴዎስ 14:3-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤ ዮሐንስ፦ እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም ይለው ነበርና። ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው።
Share
ማቴዎስ 14 ያንብቡ