ማቴዎስ 28:12-15
ማቴዎስ 28:12-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከሽማግሎች ጋርም ተሰብስበው ተማከሩና ለጭፍሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥተዋቸው “እኛ ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት” በሉ። ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለን፤ እናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን፤” አሉአቸው። እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸው አደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል።
ማቴዎስ 28:12-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የካህናት አለቆችም ከሽማግሌዎች ጋራ ተሰብስበው ተማከሩ፤ ለወታደሮቹ በቂ ገንዘብ በመስጠት እንዲህ አሏቸው፤ “ ‘ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት’ በሉ፤ ይህ ወሬ በገዥው ዘንድ ቢሰማ እንኳ፣ እኛ እናስረዳዋለን፤ ምንም ክፉ ነገር እንዳይደርስባችሁ እናደርጋለን።” ወታደሮቹም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ ታዘዙት አደረጉ። ይህም ታሪክ እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁዶች ዘንድ በሰፊው እንደ ተሠራጨ ነው።
ማቴዎስ 28:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከሽማግሎች ጋርም ተሰብስበው ተማከሩና ለጭፍሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥተዋቸው፦ እኛ ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ። ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለን እናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን አሉአቸው። እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸው አደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል።
ማቴዎስ 28:12-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች ጋር ተሰብስበው ከተማከሩ በኋላ ለወታደሮቹ ብዙ ገንዘብ ሰጡአቸውና እንዲህ አሉአቸው፤ “ ‘እኛ ተኝተን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰርቀው ይዘውት ሄዱ’ ብላችሁ ለሕዝቡ ንገሩ። ይህን አገር ገዢው የሰማ እንደ ሆነ እኛ ጉዳዩን ለእርሱ አስረድተን በማሳመን በእናንተ ላይ ችግር እንዳይደርስባችሁ እናደርጋለን። ” ስለዚህ ወታደሮቹ ገንዘቡን ተቀብለው ልክ እንደ ተነገራቸው አደረጉ፤ ይህም ነገር እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁድ ዘንድ ተስፋፍቶ ይነገራል።
ማቴዎስ 28:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከሽማግሌዎች ጋር ተሰብስበው ተማከሩና ለወታደሮቹ ብዙ ገንዘብ ሰጡአቸው፥ እንዲህም አሉአቸው፦ “‘እኛ ተኝተን ሳለን ደቀመዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት’ በሉ። ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደሆነ፥ እኛ እናሳምነዋለን፤ እናንተም ከሥጋት ነጻ እንድትሆኑ እናደርጋለን።” እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸው አደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ይወራል።