ማቴዎስ 6:20-22 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ማቴዎስ 6:20-22 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ነገር ግን ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በማይችልበት በዚያ በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት አከማቹ፤ ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያው ይሆናልና። “ዐይን የሰውነት መብራት ነው፤ ስለዚህ ዐይንህ ጤናማ ከሆነ መላው ሰውነትህ በብርሃን የተሞላ ይሆናል።
ማቴዎስ 6:20-22 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ይልቅስ ብልና ዝገት ሊያጠፉት በማይችሉበት፥ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብታችሁን አከማቹ። ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያ ይገኛል። “ዐይን የሰውነት መብራት ነው፤ ስለዚህ ዐይንህ ጤናማ ከሆነ፥ ሰውነትህ በሙሉ ብርሃን ይሆናል፤
ማቴዎስ 6:20-22 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። “የሰውነት መብራት ዐይን ናት። ዐይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤
ማቴዎስ 6:20-22 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤
ማቴዎስ 6:20-22 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ነገር ግን ብልና ዝገት በማያጠፉት፥ ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁበት በሰማይ ሃብትን ሰብስቡ፤ ሃብትህ ባለበት ልብህም በዚያ ይሆናልና። “ዐይን የሰውነት መብራት ናት። ስለዚህ ዓይንህ ጤናማ ከሆነች፥ ሰውነትህ ሁሉ የበራ ይሆናል፤