ማርቆስ 9:28-29
ማርቆስ 9:28-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ ቤትም ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ “እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምንድር ነው?” ብለው ብቻውን ጠየቁት። “ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም፤” አላቸው።
Share
ማርቆስ 9 ያንብቡማርቆስ 9:28-29 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስም ወደ ቤት በገባ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ፦ “ለመሆኑ ይህን ርኩስ መንፈስ እኛ ልናስወጣው ስለምን አልቻልንም?” ብለው ለብቻው ጠየቁት። እርሱም “እንዲህ ዐይነቱ በጸሎትና [በጾም] ካልሆነ በቀር በሌላ በምንም አይወጣም።” ሲል መለሰላቸው።
Share
ማርቆስ 9 ያንብቡማርቆስ 9:28-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢየሱስ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው፣ “እኛ ልናስወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፣ “የዚህ ዐይነቱ ሊወጣ የሚችለው በጸሎትና በጾም ብቻ ነው” አላቸው።
Share
ማርቆስ 9 ያንብቡ