ነህምያ 2:17-18
ነህምያ 2:17-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እኔም፥ “እኛ ያለንበትን ጕስቍልና፥ ኢየሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ። አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ” አልኋቸው። የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደ ሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። “ተነሡ እንሥራ” አልኋቸው። እጆቻቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።
ነህምያ 2:17-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም፣ “ያለንበትን ችግር ይኸው ታያላችሁ፤ ኢየሩሳሌም ፈርሳለች፤ በሮቿም በእሳት ጋይተዋል፤ አሁንም ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደ ገና እንሥራ፤ ከእንግዲህስ መሣለቂያ አንሆንም” አልኋቸው። እንዲሁም መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ እንደ ነበረችና ንጉሡም ምን እንዳለኝ ነገርኋቸው። እነርሱም፣ “እንደ ገና መሥራቱን እንጀምር!” ካሉ በኋላ ይህን መልካም ሥራ ጀመሩ።
ነህምያ 2:17-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እኔም፦ “እኛ ያለንበትን ጉስቁልና፥ ኢያሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ፤ አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ” አልኋቸው። የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ “እንነሣና እንሥራ” አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።
ነህምያ 2:17-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ ግን “እንግዲህ ያለውን ችግር ሁሉ ተመልከቱት! ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ሆናለች፤ የቅጽር በሮችዋም በእሳት ወድመዋል፤ ስለዚህ ተነሥተን የከተማይቱን ቅጽሮች እንሥራ፤ የደረሰብንንም ኀፍረት እናስወግድ” አልኳቸው። ቀጠል አድርጌም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑንና እንዴትም እንደ ረዳኝ፥ ንጉሠ ነገሥቱም የነገረኝን ሁሉ ገለጥሁላቸው። እነርሱም “እንደገና መሥራቱን እንጀምር!” ካሉኝ በኋላ፥ ይህን በጎ ሥራ ለመጀመር ተዘጋጁ።