ነህምያ 7:1-2
ነህምያ 7:1-2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹን አቆምሁ፤ በረኞቹንና መዘምራኑን፥ ሌዋውያኑንም ሾምሁ፤ ወንድሜን ሃናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያንም በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
ነህምያ 7:1-2 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ። በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው።
ነህምያ 7:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንዲህም ሆነ፥ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹንም ካቆምሁ በኋላ፥ በረኞቹና መዘምራኑ ሌዋውያኑም ከተሾሙ በኋላ፥ ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፥ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
ነህምያ 7:1-2 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እነሆ የቅጽሩ ግንብ ተሠርቶ አለቀ፤ የቅጽር በሮችም ሁሉ በየቦታቸው ተገጣጥመው ነበር፤ ቤተ መቅደሱን የሚጠብቁ ዘበኞች ለመዘምራን ቡድን አባላትና ለሌሎችም ሌዋውያን የሥራ ድርሻቸው ተመድቦላቸው ነበር። እኔም የኢየሩሳሌምን ከተማ ያስተዳድሩ ዘንድ ሁለት ሰዎችን ሾምኩ፤ እነርሱም የእኔ ወንድም የሆነው ሐናኒና የምሽግ ኀላፊ የነበረው ሐናንያ ናቸው፤ ሐናንያ እውነተኛና እግዚአብሔርን በመፍራት ረገድ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሰው ነበር።