ዘኍልቍ 4:7 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ዘኍልቍ 4:7 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“በገጸ ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ይዘርጉበት፤ በላዩም ላይ ወጭቶች፣ ጭልፋዎች፣ ጽዋዎች፣ ለመጠጥ ቍርባን የሚሆኑትን ማንቈርቈሪያዎች እንዲሁም ሁልጊዜ ከዚያ የማይታጣውን ኅብስት ያስቀምጡ።
ያጋሩ
ዘኍልቍ 4 NASVዘኍልቍ 4:7 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
“ለእግዚአብሔር የሚቀርበው የተቀደሰ ኅብስት ማኖሪያ የሆነውንም ገበታ በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑት፤ በገበታውም ላይ ሳሕኖችን፥ ጭልፋዎችን፥ ጽዋዎችንና የወይን ጠጅ መቅጃዎችን ያኑሩ፤ ኅብስትም ዘወትር በእርሱ ላይ ይኑርበት።
ያጋሩ
ዘኍልቍ 4 አማ05ዘኍልቍ 4:7 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
በኅብስተ ገጹ ገበታ ላይም ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ጭልፋዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለማፍሰስም መቅጃዎቹን ያድርጉበት፤ ሁልጊዜም የሚኖር ኅብስት በእርሱ ላይ ይሁን።
ዘኍልቍ 4:7 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
በገጽ ኅብስት ገበታ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ጭልፋዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለማፍሰስም መቅጃዎቹን ያድርጉ፤ ሁልጊዜም የሚኖር እንጀራ በእርሱ ላይ ይሁን።
ያጋሩ
ዘኍልቍ 4 አማ54ዘኍልቍ 4:7 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
በተቀደሰው ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ሙዳዮችንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለመጠጥ ቁርባንም መንቀሎቹን ያስቀምጡበት፤ ሁልጊዜም የሚቀርበው እንጀራ በእርሱ ላይ ይሁን።
ያጋሩ
ዘኍልቍ 4 መቅካእኤ