መዝሙር 103:3-5
መዝሙር 103:3-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እልፍኙን በውኃ የሚሠራ፥ ደመናን መሄጃው የሚያደርግ፥ በነፋስ ክንፍም የሚሄድ፥ መላእክቱን መንፈስ፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርጋቸው። ለዘለዓለም እንዳትናወጥ፥ ምድርን መሠረታት፥ አጸናትም።
መዝሙር 103:3-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣ ሕይወትሽን ከጥፋት ጕድጓድ የሚያድን፣ ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣ ጕልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።