ራእይ 6:5-6
ራእይ 6:5-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “መጥተህ እይ” ሲል ሰማሁ። አየሁም፤ እነሆም ጥቁር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ። በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ “አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ” ሲል ሰማሁ።
Share
ራእይ 6 ያንብቡራእይ 6:5-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በጉ ሦስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “ና!” ሲል ሰማሁ፤ እነሆ ጥቊር ፈረስ አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ሚዛን በእጁ ይዞ ነበር፤ ከአራቱ እንስሶች መካከል የመጣ የሚመስል ድምፅ ሰማሁ፤ ይህ ድምፅ “ግማሽ ኪሎ ያኽል ስንዴ የአንድ ቀን ደመወዝ፥ ለአንድ ኪሎ ተኩል ያኽል ገብስ ለአንድ ቀን ደመወዝ ይሁን፤ ዘይትንና ወይንን ግን አትጒዳ!” ሲል ሰማሁ።
Share
ራእይ 6 ያንብቡ