ሮሜ 14:8-9 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 14:8-9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ብንኖር ለጌታ እንኖራለን፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። ስለዚህ ብንኖርም ብንሞትም የጌታ ነን። ለዚሁ፣ የሙታንና የሕያዋን ጌታ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ ሞቷል፤ በሕይወትም ተነሥቷል።

ሮሜ 14:8-9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ብንኖር ለጌታ እንኖራለን፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን፤ ስለዚህ ብንኖርም፥ ብንሞትም የጌታ ነን። ስለዚህ ክርስቶስ ሞቶ ከሞት የተነሣው የሕያዋንና የሙታን ጌታ ለመሆን ነው።

ሮሜ 14:8-9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በሕ​ይ​ወት ብን​ኖ​ርም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ኖ​ራ​ለን፤ ብን​ሞ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ግ​ዲህ በሕ​ይ​ወት ብን​ኖ​ርም ብን​ሞ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነን። ስለ​ዚህ ሕያ​ዋ​ን​ንና ሙታ​ንን ይገዛ ዘንድ ክር​ስ​ቶስ ሞተ፥ ተነ​ሣም።

ሮሜ 14:8-9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን። ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያውም ሆኖአልና።

ሮሜ 14:8-9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን። ስለዚህ ነገር የሙታንንና የሕያዋን ጌታ እንዲሆን ክርስቶስ ሞቷልና፥ ሕያውም ሆኖአልና።