ሮሜ 3:23-26 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 3:23-26 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሏቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት እንዲያው በጸጋው ጸድቀዋል፤ በደሙም በሆነው እምነት፣ እግዚአብሔር የማስተሰረያ መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦታል፤ ይህንም ያደረገው ቀድሞ የተፈጸመውን ኀጢአት ሳይቀጣ በትዕግሥት በማለፍ ጽድቁን ለማሳየት ነው፤ በአሁኑ ዘመን እግዚአብሔር ይህን ያደረገው፣ ጽድቁን ይኸውም እርሱ ራሱ ጻድቅ ሆኖ፣ በኢየሱስ የሚያምነውን የሚያጸድቅ መሆኑን ለማሳየት ነው።

ያጋሩ
ሮሜ 3 NASV

ሮሜ 3:23-26 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሰዎች ሁሉ ኃጢአት ሠርተዋል፤ እግዚአብሔር የሰጣቸውንም ክብር አጥተዋል። ስለዚህ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው በአዳኝነት ሥራ በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ይጸድቃሉ። እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በደሙ የኃጢአታቸውን ስርየት እንዲያገኙ ነው፤ እግዚአብሔር ይህን ማድረጉ በትዕግሥቱ የቀድሞውን ኃጢአት እንዳልነበረ በማድረግ የራሱን ትክክለኛ ፍርድ ለመግለጥ ነው። በአሁኑም ዘመን እግዚአብሔር ራሱ ጻድቅ መሆኑን የሚያሳየው በኢየሱስ የሚያምኑትን ሁሉ በማጽደቅ ነው።

ሮሜ 3:23-26 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በዚ​ህም ልዩ​ነት የለም፤ ሁሉም ፈጽ​መው በድ​ለ​ዋ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማክ​በ​ር​ንም ትተ​ዋ​ልና። ጽድቅ ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ቤዛ​ነት ያለ ዋጋ በእ​ርሱ ቸር​ነት ሆነ። እር​ሱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት የሚ​ገኝ፥ በደ​ሙም የሆነ ማስ​ተ​ስ​ረያ አድ​ርጎ አቆ​መው፤ ይህም ከጥ​ንት ጀምሮ በበ​ደ​ሉት ላይ ጽድ​ቁን ይገ​ልጥ ዘንድ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታጋሽ በመ​ሆኑ፥ እሺ በማ​ለ​ቱም እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፥ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም የሚ​ያ​ም​ኑ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​ጸ​ድ​ቃ​ቸው ዛሬ ያውቁ ዘንድ ነው።

ሮሜ 3:23-26 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው።

ሮሜ 3:23-26 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ሁሉም ኃጢአትን ሠርተዋልና፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲሁ በጸጋው ይጸድቃሉ። እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን እንዲያሳይ ነው።