ሮሜ 6:22 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 6:22 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አሁን ግን ከኀጢአት ነጻ ወጥታችሁ የእግዚአብሔር ባሮች ሆናችኋል፤ የምትሰበስቡትም ፍሬ ወደ ቅድስና ያመራል፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው።

ያጋሩ
ሮሜ 6 NASV

ሮሜ 6:22 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

አሁን ግን ከኃጢአት ባርነት ነጻ ወጥታችሁ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በመሆናችሁ ቅድስናን ታገኛላችሁ፤ የቅድስናም መጨረሻ የዘለዓለም ሕይወት ነው።

ሮሜ 6:22 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ዛሬ ግን ከኀ​ጢ​አት ነጻ ወጣ​ችሁ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም ለጽ​ድቅ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፤ ለቅ​ድ​ስ​ናም ፍሬን አፈ​ራ​ችሁ፤ ፍጻ​ሜው ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ነው።

ሮሜ 6:22 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው።

ሮሜ 6:22 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አሁን ግን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ባርያዎች ሆናችኋል፥ ፍሬያችሁም ቅድስና ነው፤ መጨረሻውም የዘለዓለም ሕይወት ነው።