ሮሜ 9:19-23 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 9:19-23 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከእናንተ አንዱ፣ “ታዲያ እንደዚህ ከሆነ እግዚአብሔር እስከ አሁን ለምን ይወቅሠናል? ምክንያቱም ፈቃዱን ሊቋቋም የሚችል ማን አለ?” ይለኝ ይሆናል። ነገር ግን ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? “ሥራ ሠሪውን፣ ‘ለምን እንዲህ ሠራኸኝ?’ ይለዋልን?” ሸክላ ሠሪ፣ ከሚሠራው ጭቃ፣ አንዳንዱን ሸክላ ለከበረ፣ ሌሎቹን ደግሞ ለተራ አገልግሎት የማድረግ መብት የለውምን? እግዚአብሔር ቍጣውን ለማሳየት፣ ኀይሉንም ለማሳወቅ ፈልጎ የቍጣው መግለጫ የሆኑትን፣ ለጥፋትም የተዘጋጁትን እጅግ ታግሦ ቢሆንሳ? አስቀድሞ ለክብር ላዘጋጃቸው፣ የምሕረቱም መግለጫዎች ለሆኑት፣ የክብሩ ባለጠግነት እንዲታወቅ ይህን አድርጎ እንደሆነስ?

ያጋሩ
ሮሜ 9 NASV

ሮሜ 9:19-23 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ስለዚህ “የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመቃወም ማንም አይችልም፤ ታዲያ፥ እርሱ ሰዎችን በክፉ ሥራቸው ለምን ይወቅሳቸዋል” ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል። አንተ ሰው! ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ምን መብት አለህ? የሸክላ ዕቃ ሠሪውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ሊለው ይችላልን? ሸክላ ሠሪ ከአንድ ዐይነት የሸክላ ጭቃ አንዱን ዕቃ ለክብር፥ ሌላውን ለተራ አገልግሎት አድርጎ ለመሥራት ሥልጣን የለውምን? እግዚአብሔር ቊጣውን ለማሳየትና ኀይሉንም ለመግለጥ ፈልጎ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቊጣ ዕቃዎች ብዙ ታግሦአቸውስ እንደ ሆነ ምን ታውቃለህ? ይህንንም ያደረገው አስቀድሞ ለክብር ላዘጋጃቸው ለምሕረት ዕቃዎች የክብሩን ብዛት ለመግለጥ ነው።

ሮሜ 9:19-23 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እን​ግ​ዲህ ምን ትላ​ለህ? አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትነ​ቅ​ፈ​ዋ​ለ​ህን? ምክ​ሩ​ንስ የሚ​ቃ​ወ​ማት አለን?። ሰው ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ከ​ራ​ከ​ረው አንተ ምን​ድን ነህ? ሥራ ሠሪ​ውን እን​ዲህ አታ​ድ​ር​ገኝ ሊለው ይች​ላ​ልን? ሸክላ ሠሪ ከአ​ንድ ጭቃ ግማ​ሹን ለክ​ብር፥ ግማ​ሹ​ንም ለኀ​ሳር አድ​ርጎ ዕቃን ሊሠራ አይ​ች​ል​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ሉን የሚ​ገ​ል​ጽ​በ​ትን ቅጣ​ቱን ሊያ​ሳይ ቢወድ፥ ትዕ​ግ​ሥ​ቱን ካሳየ በኋላ ለማ​ጥ​ፋት የተ​ዘ​ጋ​ጁ​ትን ቍጣ​ውን የሚ​ገ​ል​ጽ​ባ​ቸ​ውን መላ​እ​ክት ያመ​ጣል። ዳግ​መ​ናም የክ​ብ​ሩን ባለ​ጠ​ግ​ነት ሊያ​ሳይ ቢወድ አስ​ቀ​ድሞ ለወ​ደ​ዳ​ቸ​ውና ለጠ​ራ​ቸው ለይ​ቅ​ርታ የተ​ዘ​ጋጁ የም​ሕ​ረት መላ​እ​ክ​ትን ያመ​ጣል።

ሮሜ 9:19-23 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እንግዲህ ስለ ምን እስከ አሁን ድረስ ይነቅፋል? ፈቃዱንስ የሚቃወም ማን ነው? ትለኝ ይሆናል። ነገር ግን፥ አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን ነህ? ሥራ ሠሪውን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን? ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን? ነገር ግን እግዚአብሔር ቍጣውን ሊያሳይ ኃይሉንም ሊገልጥ ወዶ፥ አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው በምሕረት ዕቃዎች ላይ የክብሩን ባለ ጠግነት ይገልጥ ዘንድ፥ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎች በብዙ ትዕግሥት ከቻለ፥ እንዴት ነው?

ሮሜ 9:19-23 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እንግዲህ “ታዲያ ለምን እስከ አሁን ስህተት ይፈልጋል? ፈቃዱን ሊቃወም ማን ይችላል?” ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል። ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን? ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንድ ዓይነት ጭቃ አንዱን ዕቃ ለክብር፥ አንዱን ደግሞ ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ መብት የለውምን? ነገር ግን እግዚአብሔር ቁጣውን ለማሳየትና ኃይሉን ለማሳወቅ ፈልጎ፥ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎችን በብዙ ትዕግሥት ተቋቁሞ ቢሆንስ? ይህም አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው በምሕረት ዕቃዎች ላይ የክብሩን ባለጠግነት እንዲገልጥ ቢሆንስ?