በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝናሙና

በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝ

ቀን {{ቀን}} ከ6

ድንጋይህን ተጠቀም

ልጅ ሳለሁ አባቴ የወፍ ማደኛ ወንጭፍ ገዝቶ ነበር፡፡ ሙያውና ልምዱ እስከሌለህ ድረስ ወንጭፉ ጥቅም አልነበረውም፡፡ የአባቴን ወንጭፍ እወደው ነበር በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ልጠቀምበት አልቻልኩም፡፡ ያን ለማድረግ ራሴን አላሰለጠንኩም ነበር፡፡

ዳዊትም ተመሳሳይ መሳሪያ ነበረው ነገር ግን ወንጭፉንና ድንጋዩን ጎልያድን ሊገጥም በወጣበት ቀን አልነበረም የጀመረው፡፡ ረጅም ዘመን ሲጠቀምባቸው፣ ክህሎቱን ሲያሳድግና ራሱን ሲያሰለጥን ስለነበር የአባቱን በጎች ሊከላከል ቻለ፡፡

ሳኦል ለዳዊት የገዛ ራሱን ልብስ፤ በራሱም ላይ የናስ ቁር መድፋቱና ጥሩር ማልበሱ የሚያስገርም ነገር ቢሆንም አልሆነም፡፡ በጣም ትልልቆችና ከባድም ነበሩ፡፡ በጎልያድ ላይ ባለ ድል አያደርጉትም ነበር፡፡ ዳዊት ወንጭፉን እንዲጠቀም እግዚአብሔር እንዳዘጋጀው ገብቶት ነበር፡፡

ዩኒቨርሲቲ እያለሁ የወንጌል ፊልሞችን ለመስራት የተነሳሳው ነበርኩኝ፡፡ ህልሜንም ዕውን ለማድረግ አስፈላጊውን መሳሪያ ለማዘጋጀት በጣም እሞክር ነበር፡፡ ኒው ዮርክ ውስጥ ወደሚገኝ የፊልም ት/ቤት መግባት እንደምፈልግ ነገርኩት፡፡ እርሱ ግን ለዚህ በቂ ገንዘብ እንደሌለው ነገረኝ፡፡ አባቴም ይህንን ፊልም የምሰራበት ምክንያት ሰዎች እንዲባረኩ እንጂ ችሎታዬን ለማሳየት እንዳልሆነ አሳስቦኝ እጄም ላይ ባለው መሳሪያዎች ራሴን እንዳሰለጥን መከረኝ፡፡ እጄ ላይ ያለኝ የነበረው ደግሞ አንድ አሮጌ ስልክ ብቻ ነበር፡፡ እግዚአብሔር እንዲያሰለጥነኝ ጠይቄው ከምገምተው በላይ መንፈስ ቅዱስ ታላቁ መምህር መሆኑን ተማርኩኝ፡፡ እናም ይህቺን ስልኬን በመጠቀም አጫጭር ፊልሞችን መቅረፅ በዩቲዩብ ላይ መልቀቅ ጀመርኩኝ በዚህም ብዙዎች ተባርከዋል፡፡ በዚያ አላቆምኩም፡፡ ሙያውን እስካጎለብት ድረስ ውስንና ደረጃውን ባልጠበቀ መሳሪያ ፊልሞችን መስራቴን ቀጠልኩኝ፡፡

ይህ መርህ በዳዊት ሕይወት ላይ ሰርቷል፡፡ ዳዊት ለጦርና ለጠመንጃ ጦርነት የተጋለጠ አልነበረም፤ እጁ ላይ የነበረውን ወንጭፍና ድንጋይ በመጠቀም እንዴት የተዋጣለት ብልሃተኛ ወደ መሆን እንደደረሰ እናያለን፡፡

በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ እየሄድን እስካለን ድረስ ከትንሹ መጀመር ለህይወታችን መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር የዕድገቱን ሂደት ቀርፆታል፡፡ ጫካ በሆነ ዘመን አንድ ዛፍ ብቻ ነበር፡፡ ያ ዛፍ ራሱ ደግሞ በሆነ ጊዜ አንድ ዘር ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ጫካውን ለመሆን ያልማሉ ነገር ግን ከዘር ፍሬው ለመጀመር ኤፈልጉም፡፡ የስልጠናህን ሂደታዊ ጊዜ አታቻኩለው፡፡ እግዚአብሔር በድንጋይ እያሰለጠነህ ሳለ አንተ ጦርን ለመጠቀም አትጣደፍ፡፡ ዳዊት በብልሃት የሳኦልን የብረት ልብስና ጦር እምቢ ብሎ አምስቱን ጠጠር መረጠ፡፡ በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች ሞኝነት ቢያስመስልም ዳዊት ግን ሁሉም ዕድሎች ወይም የተከፈቱ በሮች ከእግዚአብሔር እንዳልሆኑ ተረድቶ ነበር፡፡ ዳዊት የእድገትን መርህ በሚገባ ተረድቶ ነበር፡፡ ያ ጊዜ የጦር ጊዜ አልነበረም ምክንያቱም እሱ ኃላ ላይ ይመጣልና፡፡ ዝግጅቱን የሚመጥን ነገር አደረገ፤ ያም ድንጋይ ነበር፡፡

የዳዊት ድንጋዮች የማይስቡ፣ ያልተለመዱ የጦር መሳሪያዎች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን በእጁ ያለውን ነገር በመጠቀሙ ውጤቱ የክብር ሆነ፡፡ አንተም እንዲሁ እንድታደርግ ይጠራሃል፡፡

ቀን 4ቀን 6

ስለዚህ እቅድ

በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝ

ልክ ከኤርሚያስና ከዳዊት ህይወት እንደምትመለከተው ሁሉ ዓላማህን ለመኖር፣ እግዚአብሔርን ባለህ ነገርና ባለህበት ቦታ ለማገልገል ታናሽ አይደለህም፡፡ ለዓላማህ መዘጋጀት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ዓላማህን ሊያጠፉት ከሚያደፍጡ መጠበቅን ተማር፤ እንዲሁም ለአንድ ነገር ተዘጋጅ ይኽውም ትርጉም ያለውን ህይወት እና ዓለምን ሊባርክ የሚችለውን እግዚአብሔርን የሚያከብረውን ህይወት ለመኖር፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Mount Zion Faith Ministry ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://mountzionfilm.org/

ተዛማጅ እቅዶች