በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝናሙና

በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝ

ቀን {{ቀን}} ከ6

ዓላማህን መጠበቅ

ዲያቢሎስ አንት በእግዚአብሔር ፈቃድ እንድትሄድ አይፈልግም፡፡ የአንተን ፍፃሜ ላማጥፋት ማንኛውንም ነገር ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ዓላማህን እንዴት መጠበቅ እንዳለብህ መረዳት በጣም ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

ዳዊት ጎልያድን በማሸነፍ የእስራኤል ሁሉ አድናቆት ተመለሰ - ለሳኦል ቅር የተሰኘው - እና በሳኦል ቅናት የተነሳ የዓመታት ስጋት እና ግጭት ጀመረ። ዳዊት ጎልያድን አሸንፎ ሲመለስ ድፍን እስራኤል አሞገሰው፤ ሳኦል ግን በሙገሳው ደስ አልተሰኘም፤ ይህ የሳኦል ቅንዓት ለዓመታት ስጋትና ግጭት እንዲጀመር ምክንያት ሆነ፡፡ ሳኦል የዳዊትን ዓላማ ለማጥፋት ቆርጦ ነበር፡፡ የገዛ ልጁ ዮናታን ለዳዊት የልብ ወዳጅ ሆኖ፤ የአባቱ ሳኦል ሃሳብ ገብቶት ዳዊትን ሊገድለው እንዳቀደ አውቆ ከፊቱ እንዲሸሽ ያደርገዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ዓላማ እንደተሸከመ ሰው አንተም ዓላማህን ከሚያቃልሉብህ፤ ፍፃሜህን ሊያጠፉ ከሚሹ ሰዎች ማምለጥ ያስፈልግሃል፡፡ እግዚአብሔር አንተን ከየት እንዳመጣህና ወደየት እየወሰደህ እንዳለህ ማንም ሰው ሊረዳው አይችልም፡፡

ልክ እንደ ዳዊት በየምድረበዳው ልትንከራተት ትችላለህ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አንተን እያሰለጠነ፤ ከአንተም ምቹ ሁኔታህ ላይ መወገድ የሚገባውን ለማስወገድ አንተን ለማይመች ነገር ያጋልጥሃል፡፡ ይህ ዓላማህን ለማጥፋት ሳይሆን አንተን ለመቅረፅ ነው፡፡ እውነተኛው ክብሩ እስኪያንፀባርቅ ድረስ ወርቅ በእሳት ውስጥ ያልፋል፡፡ ልክ እንደዛው እግዚአብሔርም አንተን ለዓለም ከመግለጡ በፊት በእሳት ውስጥ ታልፍ ዘንድ ይፈቅዳል፡፡ በእሳትና በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ አብሮህ ለመሆን ተስፋ የሰጠህ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

የእግዚአብሔርን ዓላማ በህይወትህ ለመጠበቅ የመጀመሪያው እርምጃህ ቃሉን ማጥናትና ለቃሉም እውነተኛ ሆኖ መቆየት ነው፡፡ ለዳዊት እንደሆነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ለእግርህ መብራት ለመንገድህ ብርሃን ነው፡፡ የዲያቢሎስን ውሸት ላለማመን ንቃ! ስለ አንተ ዓለም የሚለው አንተ ማን እንደሆንክና እግዚአብሔር ወዴት እየወሰደህ እንዳለ በፍፁም አይገልፅም፡፡ ዓላማህን በእርግጠኝነት የመጠበቂያው መንገድ በፍፁም ልብህ የሰማዩ አባትህ ስለ አንተ በቃሉ በኩል ባለህ ላይ በማመን ነው (ማህበራዊ ሚዲያው ስለ አንተ በሚለው ላይ አይደለም)፡፡

በሁለተኛነት ደግሞ ለምክር የመገዛትንና የመታዘዝን ውበት ተማር፡፡ በህይወት ጎዟቸው ትንሽ ከአንተ የቀደሙ ሰዎች የሚያበረታታ ቃል ያስፈልግሃል፡፡

በሦስተኛነት ደግሞ ለአገልግሎት ተገኝ፡፡ ለማገልገል በጣም ትልቅ ከሆንክ ለመምራት ደግሞ በጣም ትንሽ ነህ፡፡ ሁሉም ታላላቅ ሰዎች የሆነ ዘመን አገልጋዮች ነበሩ፡፡ ዳዊት እንኳን በአንደ ወቅት የእስራኤልን ንጉስ አገልግሎ ነበር ኋላ ግን ራሱ ንጉስ ሆነ፡፡ ህልምህ ታላቅ ሙዚቀኛ መሆን ከሆነ በአጥቢያ ቤተክርስቲያንህ የሙዚቃ ዘርፍ ውስጥ ገብተህ ማገልገል አለብህ፤ በትንሹም ቢሆን፡፡

በአራተኛ ደረጃ ደግሞ ትሑት ሁን፡፡ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ፀጋን ይሰጣል፡፡ እኛ እግዚአብሔርን በትህትና ስናምነው በጊዜና በሰዓቱ ከፍ ያደርገናል፡፡

በዚህ በምድር ፍፃሜ በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ በደስታ እንድትጓዝ ብርሃንህ ይብራ፡፡

ቀን 5

ስለዚህ እቅድ

በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝ

ልክ ከኤርሚያስና ከዳዊት ህይወት እንደምትመለከተው ሁሉ ዓላማህን ለመኖር፣ እግዚአብሔርን ባለህ ነገርና ባለህበት ቦታ ለማገልገል ታናሽ አይደለህም፡፡ ለዓላማህ መዘጋጀት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ዓላማህን ሊያጠፉት ከሚያደፍጡ መጠበቅን ተማር፤ እንዲሁም ለአንድ ነገር ተዘጋጅ ይኽውም ትርጉም ያለውን ህይወት እና ዓለምን ሊባርክ የሚችለውን እግዚአብሔርን የሚያከብረውን ህይወት ለመኖር፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Mount Zion Faith Ministry ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://mountzionfilm.org/