እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶችናሙና
የጴጥሮስ ጌታን መካድ
በፋሲካ ዋዜማ ታሪክ ውስጥ በጣም የተዘነጋው የሐዋሪያው ጴጥሮስ ጌታን የካደበት ታሪክ ነው፡፡ ይህ የዋዜማው የጴጥሮስ ውድቀት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ከተጠቀሱት በጣም ጥቂት ታሪኮች አንዱ ስለሆነ፡፡
ለእኔ የሚመስለኝ ይህ ታሪክ እጅግ ወሳኝ ነው ምክንያቱም እንደ ክርስቲያን ያለንን ውድቀት በወንጌል መነጽር ያሳየናል፡፡ ይህ ታሪክ በመጀመሪያ የሚያስተምረን እግዚአብሔር እንደ ክርስቲያን ያለንን የውድቀት እውነት እውቅና እንደሚሰጠው ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የሚያስተምረን ደግሞ እግዚአብሔር እንደ ክርስቲያን ያለንን ውድቀቶች አስቀድሞ ማወቁን ነው፡፡ በሦስተኛ ደረጃ በዋነኛነት ደግሞ ይህ ታሪክ የሚያስተምረን እግዚአብሔር እንደ ክርስቲያን ባለን ውድቀቶች ይቅር እንደሚለን ነው፡፡
በዚህ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ እንደ ክርስቲያን እያንዳንደቸውን ውድቀቶች በወንጌል መነጽር እንመለከታቸዋለን፡፡ ይህ ከእግዚአብሔር ጋር በምናደርገው ጉዞ፣ እግዚአብሔር እንድንሆንለት በሚፈልገውና በምናውቀው ውድቀት እንዲሁም እኛም ልንሆን በምንፈልገውና በወደቅንበት ጉዳይ በጣም የሚያበረታታን ነው፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ይህ የሚያበረታታ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ የሚዳስሰው እውነት በሉዓላዊነቱ እግዚአብሔር የእኛን ውድቀት አስቀድሞ ያያል እንዲሁም በርህራሄው ደግሞ ውድቀቶቻችንን ይቅር ይላል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/