እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶችናሙና
![እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶች](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans-staging%2F50492%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
አስቀድሞ የታወቀ
ማቴዎስ ሲዘግብ ኢየሱስ ከመካከላቸው አንዱ እንደሚክደው ለደቀ-መዛሙርቱ ነግሯቸው ነበር ይለናል፡፡ ደቀ-መዛሙርቱ ይህንን ሲሰሙ እጅግ ደንግጠው ነበር፡፡ ሲመልሱም “እኔ በፍፁም ልሆን አልችልም፤ እኔ አይደለሁም” እያሉ ነበር፡፡
እንደገና ኢየሱስ ለደቀ-መዛሙርቱ “በዚህች ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ትሰናከላላችሁ” እነርሱ ደግሞ “አይሆንም! አይሆንም! አይሆንም! በፍጹም እኛ አንሆንም!” ብለው ሁሉም መለሱ፡፡ በጊዜው ማንም ይሁዳን አልጠረጠረውም፡፡ ጴጥሮስ ሲመልስ “እኔ በፍጹም! ሁሉ ቢተውህ እኔ በፍጹም አልተውህም! ጌታ ሆይ እኔን ታውቀኛለህ፤ እኔ ልሞትልህ ተዘጋጅቻለሁ፡፡” አለ፤ እየሱስ ግን ሊሆን ያለውን አይቶ ጴጥሮስ ዶሮ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ እንደሚተወው ተናገረ፡፡
በሌላ አገላለጽ የይሁዳ፣ የጴጥሮስና የሌሎች ደቀ-መዛሙርት ውድቀት በጌታ አስቀድሞ የታየና የታወቀ ነበር፡፡ በሚደንቅ ሁኔታ ዮሐንስ ሲዘግብ ክርስቶስ ጴጥሮስ እንደሚክደው ለጴጥሮስ ከነገረው በኋላ ወዲያው ለጴጥሮስና ለሌሎች ደቀ-መዛሙርት “ልባችሁ አይሸበር በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ፡፡” ብሎ ሲያጽናናቸው እናያለን፡፡
ክርስቶስ ሁሉም ሊተዉት እንደሚችሉ አስቀድሞ እያወቀ ከተናገራቸው የእውነት አስገራሚ ቃላት ናቸው፡፡ ክርስቶስ ለደቀ-መዛሙርቱ ይህንን ሲናገር እያላቸው ያለው፡
ከእናንተ አንዱ አሳልፎ እንደሚሰጠኝና ከእናንተ አንዱም እንደሚክደኝ፤ እንዲሁም ሁላችሁም እንደምትተውኝ በሚገባ አውቃለሁ፡፡ ግን ሁሉም ተመሳሳይ ስለሆነ እኔም ስለ እናንተ ልሞትላችሁ ወደ መስቀል እየሄድኩኝ ስለሆነ ልባችሁ አይሸበር፡፡
ታዲያ አያስገርምም?
በማጠቃለያ እግዚአብሔር ይመስገን! እንደ ክርስቲያን ማንኛውም ውድቀቶቻችን አስቀድመው በምንም ሁኔታበእግዚአብሔር የታዩና የታወቁ ናቸው፡፡
ስለዚህ እቅድ
![እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶች](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans-staging%2F50492%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
ይህ የሚያበረታታ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ የሚዳስሰው እውነት በሉዓላዊነቱ እግዚአብሔር የእኛን ውድቀት አስቀድሞ ያያል እንዲሁም በርህራሄው ደግሞ ውድቀቶቻችንን ይቅር ይላል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/