እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶችናሙና
ይቅር ተብለናል
ሉቃስ ሲጽፍ ክርስቶስ ጴጥሮስን ሶስት ጊዜ እንደሚክደው ከማስጠንቀቁ በፊት ክርስቶስ ለጴጥሮስ እንዲህ አለው “ስምዖን ስምዖን ሆይ፣ እነሆ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና”፡፡ ጴጥሮስም እንዳየነው ክርስቶስን ለመካድ ሄደ፡፡ የጴጥሮስ ብርታት ጠፋ፤ ከይሁዳ እምነት በተለየ ግን የጴጥሮስ እምነት አልጠፋም ነበር፡፡
በዮሐንስ ወንጌል መጨረሻ አከባቢ የትንሣኤው ክርስቶስ ከየት እንደመጣ ሳይታወቅ ድንገት በገሊላ ሀይቅ አጠገብ ተገኘ፡፡ በተዓምራቱም እጅግ ብዙ ዓሳዎችን እንዲይዙ አድርጓቸው በውሃ ዳርቻ ቁርስ አዘጋጀላቸው፡፡
ሁሉም ከበሉ በኋላ ከሀይቁም ሊሄዱ ጉዞ በጀመሩ ጊዜ ክርስቶስ ጴጥሮስን ይህን ጥያቄ ጠየቀው “ጴጥሮስ፤ ትወደኛለህን?” ብሎ፡፡ ይህን ጥያቄ ክርስቶስ ልክ ሶስት ጊዜ ጴጥሮስን ጠይቆት እንደካደው ዓይነት ጥያቄ ደግሞ ሶስት ጊዜ ጠየቀው፡፡
እኔ እንደማምነው ክርስቶስ ይህን ያደረገበት ምክንያት ምንም እንኳን በሊቀ-ካህኑ ግቢ አቅሉን ቢስትም የጴጥሮስ ዕምነትና ደህንነት እንዳልጠፋ ሊያረጋግጥለት ነው፡፡ እርሱ የጴጥሮስን ጥፋተኝነት፣ ውድቀት፣ ውርደት፣ ሀፍረት፣ መዋረድ እና ኃጢአት በእርሱ ላይ ተሸክሞ መስቀሉ ላይ የዋለ የትንሳኤው ክርስቶስ ነው፡፡
የትንሳኤው ክርስቶስ “መቼም አልክድህም ያልከኝ መስሎኝ ነበር?” አንተና እኔ ያደረግነው ግን ይህ ነው፤ አይደለም? ብሎ አላሳጣውም፡፡ ክርስቶስ ጴጥሮስን ባለመኮነን ዮሐንስ በወንጌሉ እግዚአብሔር በዓለም ላይ እንዲፈርድ ልጁን ወደ ዓለም አልላከውም ነገር ግን በእርሱ ሊያድን እንጂ የተባለውን እያረጋገጠ ነው፡፡ ክርስቶስ ጴጥሮስን አልኮነነውም ምክንያቱም እርሱ ጴጥሮስን ለመኮነን ሳይሆን ሊያድነው ነበር የመጣው፡፡
ወንድሞቼና እህቶቼ ሆይ ክርስቶስ ውድቀታችንን፣ የእኛን ጥፋት እና ሀፍረታችንን በመስቀሉ ላይ ተሸክሞልናል፡፡ ልክ እኛ ዕምነታችንን ክርስቶስ በሰራልን በመስቀሉ ላይ ስናኖረው እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ሁሉ ይቅር ይለናል፣ ቅዱስ መንፈሱም የክርስቶስን የትንሳኤ መንፈስ እያካፈለን እና ኃጢአትን እምቢ እንድንል አቅም ሊሰጠን በውስጣችንን ይናራል፡፡
ክርስቶስ ለሰራነውም ሆነ ወደፊትም ለምንሰራው ኃጢአት አንዴ ሞቷል፡፡ ኃጢአት እንዳደረግን መንፈስ ቅዱስ ሊያሳስበን ሲወቅሰን ያን ኃጢአት ባለመካድ ነገር ግን በክርስቶስ የእኛ የሆነውን ይቅርታ በዕምነት መቀበል አለብን፡፡ ለዚያ ነው ጳውሎስ አንዱ የወንጌል የክብር ተስፋ እግዚአብሔር ሁሉን በሚያዩ ዓይኖቹ እንደዳንን የሚያሳስበን ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለ እኛ ከደህንነታችን በፊትም ሆነ ኋላ እጅግ አስከፊውን ነገር ስለሚያውቅ በክርስቶስ እኛን ለማዳን የወሰነው ውሳኔ በማንም ሊለወጥ የማይችል የመጨረሻ ውሳኔ ነው፡፡
ስናጠቃልል ስለ ውድቀቶቻችን ያለውን እውነታ የሚያውቀው እንዲሁም አስቀድሞ ውድቀቶቻችንን የሚገነዘበው እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በወንጌሉ ኃጢአታችንን በእጅጉ ይቅር ይለዋል፡፡
ስለዚህ እቅድ
ይህ የሚያበረታታ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ የሚዳስሰው እውነት በሉዓላዊነቱ እግዚአብሔር የእኛን ውድቀት አስቀድሞ ያያል እንዲሁም በርህራሄው ደግሞ ውድቀቶቻችንን ይቅር ይላል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/