እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶችናሙና

እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶች

ቀን {{ቀን}} ከ5

የወንጌል ምልከታ ስለውድቀታችን

ጴጥሮስ ለኢየሱስ “ሌሎቹ ሁሉ ትተውህ ቢሄዱ እኔ ግን አልተውህም” ብሎ በራሱ ጥንካሬና መልካም ሃሳብ ተደግፎ ይህንን ትልቅ የኃጢአት ፈተና ለመቋቋም ሲጥር ነገር ግን የጴጥሮስ በራስ መደገፍ ውጤት ውድቀቱ ሆነ፡፡

ነገር ግን ከጥቂት ወራት በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልቶ ጴጥሮስ በአይሁድ የሀይማኖት አለቆች ሁሉ ፊት ቆመ፡፡ ወንጌሉን መስበክ ያቆም ዘንድ ቢጠይቁትም እርሱ ግን በታላቅ ድፍረት እነርሱን ከመታዘዝ እግዚአብሔርን መታዘዝ እንዳለበት ያውጅ ነበር፡፡ ጴጥሮስ ከዚህ በፊት ለውድቀት የዳረገውን በራስ ጥንካሬና በጎ ሀሳብ መደገፍ አቁሟል፤ ይልቅ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከሞት በተነሳው ክርስቶስ ላይ መደገፍ ጀምሯል፡፡

ይህ የሚያሳየን ለኃጢአትና ለውድቀት የሚዳርገን ፈተና ሲገጥመን በፀሎት ጌታን መጥራትና በእርሱም ላይ በመደገፍ እንድናልፍ ነው፡፡

ክርስቲያን ለመሆን መጀመሪያ ማድረግ ያለብን ነገር መውደቃችንን አምነን ለእግዚአበሔር መናዘዝ አለብን፡፡ ነገር ግን አንዴ ክርስቲያን ከሆንን ወዲህ የመጨረሻ ማድረግ የሚገባን ነገር አሁንም ልንወድቅ እንደምንችል ማመን አለበን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከዚህ በፊት በወደቅንበት ተመሳሳይ ኃጢአት ስንወድቅ ለመቀበል ይቸግረናል፡፡

ዘወትር የምናስብበትን ሁኔታዎች፤ ወይም ደግሞ በራሳችን ስንሆን የምንመለከተውን ምልከታ፣ አልያም ደግሞ አንዳንዴ ከእኛ ያነሱ ናቸው ብለን የምናያቸውን ሰዎች የምንንከባከብባቸው ሁኔታዎችን ለመቀበል ሲከብደን ስናይ ያ በክርስቲያናዊ መርሆች ለመመራት ሲሳነን መሆኑን ያሳያል፡፡

ለአንዳንዶቻችን የወደቅንበት ሁኔታ ምናልባትም ጥልቅ የሆነ ሀፍረት ወስጥ ከቶናል፡፡ ግን አንድ ነገር አስታውስ ጴጥሮስ እንደነበረው አንተ በሊቀ-ካህኑ ግቢ ውስጥ አይደለህም፡፡ ደግሞም አስታውስ አንተ በፍርድ አይደለህም፤ ምክንያቱም ስለአንተ ወደ ፍርድ ሄዶልሃልና፡፡

እንደ ክርስቲያን አንተ አሁን በየቀኑ አስቀድሞ ውድቀትህን በሚያውቀው በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ነህ፤ እስካሁንም አድኖሃል፡፡ ይህ ታላቁ የወንጌል የምስራች ነው፡፡ መንፈሳዊ ብስለትን ወደ ሚያመጣው፤ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ደግሞ ዘወትር ስራውን እየሰራን ለመቀጠል ልክ ጴጥሮስ እንዳደረገው በክርስቶስ የአንተ የሆነውን ይቅርታ በዕምነት መቀበልና ጌታን ማመን ትችላለህ፡፡

አንድ በጣም ማስታወስ የሚገባን ነገር ምንም እንኳን በጌታ ይቅር የተባሉ ቢሆኑም እንኳን ውድቀቶቻችንን ነው፤ ምክንያቱም የችግር ወጀቦችን አስከትለው ሊመጡ ይችላሉና ነው፡፡ መልካሙን ስማችንንና ግንኙነቶቻችንን ሊያበላሹ ወይም በሕይወታችን ላይ ያልተገባን ነገር ጥለው ያልፋሉ፡፡ ለምሳሌ የጴጥሮስ ታረክ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲታወስ ሁልጊዜ ጌታን የካደበት ዘገባ እንደ ጉድፍ ይተረካል፡፡ ውድቀቶቻችን ቤተሰቦቻችንን ያሳዝናል፤ እንደ ልጆቻችን ላሉ እኛን ለሚመለከቱ ደግሞ መጥፎ ምሳሌ ያስደርገናል፡፡ የእኛ ውድቀት አማኞች ባልሆኑት ዘንድ ደግሞ ክርስትና እንዲነቀፍ ያደርገዋል፡፡

ስለዚህ እባካችሁ እንደ ክርስቲያን ኃጢአትንና ውድቀትን አቅልለን ለመመልከት አንድፈር፤ ምክንያቱም በዚህ ክፍል እንደምንረዳው ደጋግመን እንደ ጴጥሮስ በወደቅን ቁጥር በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እኛም ጌታን እንክደዋለን፡፡

ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶች

ይህ የሚያበረታታ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ የሚዳስሰው እውነት በሉዓላዊነቱ እግዚአብሔር የእኛን ውድቀት አስቀድሞ ያያል እንዲሁም በርህራሄው ደግሞ ውድቀቶቻችንን ይቅር ይላል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/