የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ጋብቻናሙና

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ጋብቻ

ቀን {{ቀን}} ከ3

5ቱ የጋብቻ ዓላማዎች

በእግዚአብሔር ሀሳብ ውስጥ ያለውን አስደናቂውን በወንድና በሴት መካከል ስላለው የህይወት ዘመን ጓደኝነት በጥልቀት ለመረዳት የሚከተሉትን 5ቱን የጋብቻ ዓላማዎች መመልከት ያግዘናል፡፡

የመጀመሪያው ዓላማ ባለፉት ሁለት ቀናት እንዳነበብነው ጓደኝነት ነው፡፡ አዳም ሔዋን ጋር ከመድረሷ በፊት በኤደን ገነት የአትክልት ስፍራ ለእርሱ በጣም መልካም ነገሮች እየሆኑለት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አልነበረም፡፡ እርሱ ልብ ይበለውም አይበለው ልክ እንደ እርሱ የሆነች ግን ልዩ ረዳት አጋር አስፈልጎት ነበር፡፡

ሁለተኛው የጋብቻ ዓላማ መብዛት ነው፡፡ እግዚአብሔር አዳምንና ሔዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ ባረካቸው፡፡ በተለያየ ምክንያት አንዳንድ የተጋቡ ጥንዶች ልጆች ላይኖራቸው ይችላል ጋብቻና ቤተሰብ ግን ለሰው ዘር ፍጥረት የእግዚአብሔር ሀሳብና ዕቅድ ነው፡፡

ሦስተኛው የጋብቻ ዓላማ አዋጅ ነው፡፡ ጋብቻ ህያው የሆነ የክርስቶስና የቤተክርስቲያን ምሳሌነት ምልክት ነው፡፡ የተጠራንለትን የኢየሱስን ፍቅርና ታማኝነት ለዓለም ለማሳየት በጋብቻ ውስጥ ያለን ፅናት፣ አንድነት እና የልብ ለልብነት በጣም ወሳኞች ናቸው፡፡

አራተኛው የጋብቻ ዓላማ ንጽህና ወይም ቅድስና ነው፡፡ እግዚአብሔር አስደናቂውን የወስብ ስጦታ ሲያበጅ እጅግ በሚመቸውና ቅዱስ በሆነው ጋብቻ ውስጥ ብቻ እንዲተገበር ነው፡፡ ጋብቻ እግዚአብሔር እኛን ከዝሙትና ከአመንዝራነት ሊታደገን ያመቻቸልን ቦታ ነው፡፡

አምስተኛው የጋብቻ ዓላማ ዕርካታ ነው (ይህም ከንጽህና ጋር ይያያዛል)፡፡ አንዱ አስደናቂው የጋብቻ በረከት ምቹ በሆነ፣ ደህንነቱ በተጠበቀ እና በማይዋዥቅ ሁኔታ በአካላዊ አንድነት ውስጥ የሚገኝ የደስታ ዕድል ነው፡፡ በጋብቻ ውስጥ እንዳለው መተማመንና ፍቅር የሞላበት ዓለም ከሌላ ሰው ጋር ወሲብ ቢፈፀም ግልፅ እንዲሆንና እንዲታወቅ አይፈለግም፡፡ ለዚህ ነው አለመታመን በጣም የሚቆረቁረው፡፡ ይህ የልብ በሆነልህ ሰው ላይ ክህደት መፈፀም ነው፡፡

ጋብቻ በመልካምነት ከተንበሸበሸው ፈጣሪያችን የመጣ አስገራሚ ስጦታ ነው፡፡ በተቻለን ሁሉ ጋብቻን ለማክበር እንጣር ይኸውም እንዴት እንደምንናገር፣ እንዴት እንደምንይዘው፣ እንዴት በውስጡ እንደምንኖርና እንዴት በውስጡ ያሉትን ከማበርታት ጭምር ነው፡፡ ይህንን የምናደርገው ምክንያት ደግሞ ጋብቻ ከእግዚአብሔር ስለመጣና ስለ እግዚአብሔርም ስለሚያወራ ነው፡፡ ጋብቻ ክርስቶስ ለቤተ-ክርስቲያኑ ያለውን ፍቅርና ታማኝነት ዓይነት ለአንድ ሰው ብቻ በታማኝነትና በፍቅር በህይወት ዘመን ሁሉ መሰጠት ያለበት ቦታ ነው፡፡ ይህንን ታላቅ ስጦታ ለሰጠን ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን፡፡

ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ጋብቻ

ያገባህም/ሽም ሁን/ኚ ልታገባ/ቢ የምትፈልግ/ጊ ይህ የ3 ቀናት የንባብ ዕቅድ በህይወት/ሽ ዘመን ላለው የባልነት ወይም የሚስትነት መሰጠት የእግዚአብሔርን መልካም ዓላማ እንድታውቅ/ቂ ይረዳሃል/ሻል፡፡ የጥምረትን፣ መብዛት፣ የአዋጅን፣ የቅድስናንና የእርካታን ዓላማዎች በመፈለግ ኢየሱስ ለሙሽሪት ቤተ-ክርስቲያኑ ያለውን ፍቅር ማንፀባረቅን ተማር፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Kip' Chelashaw ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://christchurchke.org/

ተዛማጅ እቅዶች