የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘረኝነትና የእኛ ምላሽናሙና

ዘረኝነትና የእኛ ምላሽ

ቀን {{ቀን}} ከ4

ዘረኝነትና መንፈሳዊነት ጉዳይ ነውን?

በተለያዩ ግንባሮች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ዓለም ታይቶ የማይታወቅ ቀውስና አሳዛኝ ነገሮች ገጥሟታል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛው ከዘረኝነት ጋር የተያያዘ ሲሆን ውጤቱም እጅግ ልብ ሰባሪ ነው፡፡ አይተህም ይሁን ደርሶብህ ግን ዘረኝነት ሁላችንንም ነክቶናል፡፡ ዘረኝነት ከየት እንደመጣ፤ ለምንስ የሰው ዘር ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ እርስበርስ እንደሚጨካከን መረዳት አስቸጋሪ ነው፡፡ በርግጥም በርዕሰ-ጉዳዩ ላይ የእያንዳንዱ ሰው ተሞክሮና መረዳት ይለያያል፡፡ የዚህን ስረ-መሰረት ለመረዳት የእኛን ሰውኛ ምልከታ ጥለን የሁሉ ነገር ጅማሮና መነሻ ወደ ሚሆነው ወደ እግዚአብሔር ቃል መዞር ያስፈልገናል፡፡

እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ ፈጥሮታል፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ ግለሰብ በአምሳሉ እርሱን እንዲያንጸባርቅ በእግዚአብሔር መልክ ነው ስለተፈጠረ አኛ ሁላችን የውስጥ ዕሴትና ጠቀሜታ አለን፡፡ ሁላችንም አክብሮት፣ ክብር፣ ፍቅር፣ ጸጋ፣ ተቀባይነት እና መደመር ይገባናል፡፡ በግልጽም ይሁን በስውር ልክ የእግዚአብሔርን መልክ እኛ የሰጠን ይመስል ሰዎችን ስናኮስስ እንገኛለን፡፡ ዘረኝነት የሚጀምረው የእግዚአብሔርን መልክ እኛን በማይመስሉን ሰዎች ላይ ማየት የተሳነን ጊዜ ነው፡፡ የሚገርመው ሌሎች ሰዎች መቼም ቢሆን እኛን እንዲሆኑ አይጠበቅም፡፡ እኛ እንድንሆን የሚጠበቀው እንደ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ ዘረኝነትን የግብረ-ገብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም መሆኑን ያሳያል፡፡

በዘር ጉዳይ ላይ የተሃድሶና የማስታረቅ አማራጮች የሚጠቅሙና አሰፈላጊ ቢሆኑም ነገር ግን ዘረኝነትን በመንፈሳዊ ደረጃም ለመታገል ጊዜው ነው፡፡ ሰዎቸን ልክ እግዚአብሔር እንደሚያይ በፀጋና በፍቅር መነፅር ማየትን መማር ያስፈልገናል፡፡ የራዕይ መጽሐፍ መንግስተ ሰማይ ምን ልትመስል እንደምትችል ስዕል ይሰጠናል፤ ይኸውም ከተለያዩ ጎሳና ነገድ የተዋጁ የእግዚአብሔር ህዝቦች የማይመሳሰሉ ግን አንድ የሆኑበት መሆኑን ነው፡፡ ልክ ኢየሱስ ሲፀልይ በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር መንግስት በምድም በሰዎች መካከል ትሆን ዘንድ እንደፀለየው መፀለይ አለብን፡፡

በመጨረሻም ኢየሱስ ዕንባን ሁሉ ከዓይናችን ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህም ሞት፣ ሀዘን፣ ለቅሶ ወይም ህመም ፈፅሞ አይኖርም፡፡ እስቲ ለቅጽበት ፍትህ ማጣት፣ መገለል፣ ጥላቻ፣ ጭፍን ፍረጃና ነቀፋ በአንድ ጀምበር የተወገዱባትን ነገን ሳልና ህይወትህ እንዴት የተለየ ሊሆን እንደሚችል አስብ፡፡ ሁሉን አዲስ የሚያደርገውን ኢየሱስን በመጠባበቅ እግዚአብሔር የሚፈልገው ዓይነት ኑሮ እየኖርን፣ ሰዎችን ሁሉ ወደ ሰፊው ቦታ የሚወስደውን የአንድነትን፣ የፍቅርን እና የፀጋን ድልድይ ለመገንባት እንሰራለን፡፡ እኛ ለማደስና ለተሃድሶ የእግዚአብሔር ንድፍ ስለሆንን ከዘር ፍትሐዊነት ጋር በተገናኘ እጅግ ንቁ እንድንሆን ያነሳሳናል፡፡

ስናጠቃልል የዘረኝነት ስሩ መንፈሳዊ ነው፡፡ እኛን በማይመስሉን ሰዎች ላይ የእግዚአብሔርን መልክ ማየት አቁመናል፡፡ እግዚአብሔር በመንገድ ላይ ስናልፍ የምናያቸውን ሰዎች፣ አብረናቸው የምንሰራቸውን፣ አብረናቸው የምናጠናቸው ወይም በቤተ-ክርስቲያን አብረን የምናገለግላቸው ሰዎችን ውበት ማየት እንድንችል ዓይኖቻችንን እንዲከፍት እንጠይቀው፡፡ ልክ የታላቁ እግዚአብሔር መልክ እናዳለባቸው፤ ክብሩንም በልዩነቶቻቸው ላይ እንደገለጠባቸው ፍጥረት ፍቅርን፣ ክብርንና አክብሮትን ለእነርሱ ለመግለፅ የትኛውንም ዕድሎች መፈለግ መቻል አለብን፡፡

ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

ዘረኝነትና የእኛ ምላሽ

እንደ ክርስቲያን በዙሪያችን ባለው ዓለም ያለውን የዘረኝነት ውጤትና የእኛን ምላሽ መመልከት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ጊዜውን የጠበቀ እጅግ አስደሳች የአራት ቀናት ዕቅድ የዘረኝነትን ስር እንዲሁም በዚህ ዓለም በእግዚአብሔር የመዋጀትና የተሃድሶ ስራ ውስጥ እንድንጫወት የተጠራንበትን ጉዳይ ይዳስሳል፡፡ ይህ ዕቀድ የተዘጋጀው በዩቨርዥን ነው፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Sidhara Udalagama ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.linkedin.com/in/sidhara-udalagama-b89b32210/?originalSubdomain=au

ተዛማጅ እቅዶች