የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘረኝነትና የእኛ ምላሽናሙና

ዘረኝነትና የእኛ ምላሽ

ቀን {{ቀን}} ከ4

ሒዱና አድርጉት

ዕውቀት ልክ እንደ ቀለም ነው ስንጠቀመው ነው ውጤታማ የሚሆነው፡፡ ሁላችንም ራሳችንን እንደምንወድ ሌሎችን መውደድ እንዳለብን ዕውቀቱ አለን፤ ነገር ግን ያንን ዕውቀት ተግባራዊ ካላደረግነው ግን ምንም አይቀየርም፡፡ ምን መምሰል እንዳለበት ትልቅ ምሳሌያችን ኢየሱስ ነው፤ ይህም ምን መደረግ እንዳለበት ለማወቅ ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት ለመዘርጋትና ለማድረግም ጭምር ነው፡፡

በእግዚአብሔር የማስታረቅና የመዋጀት ታሪክ ውስጥ የምንጫወተው ሚና የግድ ጉልህ ሆኖ ትልቅ መሆን አይጠበቅበትም፡፡ ለብዙዎች ልናደርግ የምንመኘውን ነገር ለአንዱ ማድረግ እንችላለን፡፡ ወሳኙ ነገር አንድ ነገር ማድረግ እንችላለን የሚለው ነው፡፡ ኢየሱስ የደጉ ሳምራዊውን ምሳሌ ሲቋጨው “እናንተም ሒዱና እንዲሁ አድርጉ” በማለት ነው፡፡ ለእኛ ይህ ትዕዛዝ ማለት የኢየሱስን የልብ ትርታ ማንፀባረቅና በምድር ላይ የእግዚአብሔርን መንግስት መመስረት ማለት ነው፡፡ ወደ ዘረኝነት ስናመጣው ታዲያ ለሰው ዘር ሁሉ ዋጋ እንሰጣለን፣ እያንዳንዱም ሰው በእግዚአብሔር መልክ መፈጠሩን እንረዳለን ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ሰዎችን ልክ እግዚአብሔር እንደሚያየው ውቦች እንደሆኑ፣ ዋጋ እንዳላቸው፣ ተቀባይነት እንዳላቸው እንዲሁም ለታላቅነትና ለዓላማ መፈጠራቸውን ማየትን መማር ነው፡፡

ያ ሳምራዊ ያንን የቆሰለውን ተጓዥ ባየው ጊዜ ቆሞ ብቻ አላየውም ነገር ግን እጅግ ብዙ ጊዜ ወስዶ፣ ገንዘብ፣ ልፋት እንዲሁም ተጎጂውን ሰው ለመውሰድና አካላዊ ፍላጎቱንም ለማሟላትና ለመንከባከብ ኃይሉን አውጥቷል፡፡ እስቲ በቅፅበት በአሁኑ ወቅት በዙሪያ ያሉትን የሰዎችን ቁጥር ግምት አስላ፡፡ ነገ ወይም በሚቀጥለው ወር ምን ሊያስከፍልዎት ይችል ይሆን - ፍትሐዊ ባልሆነ ሁኔታ ለተዳኘ እንድንቆምለት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊና አካላዊ ፍላጎትን ጭምር ማሟላት ይሆን? ዋጋህን ለመተመን በምድር ላይ የእግዚአብሔር የተሃድሶ እቅድ አካል መሆንህን እንዴት ነው የምታውቀው?

ቀላል ወይም በብዙዎች ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል ነገር ግን የደጉ ሳምራዊውን ፈለግ መከተል ግን ያስፈልገናል፡፡ ዋጋችንን በመተመን ኢየሱስን በዓለማችን ለማንፀባረቅ ቃል ከሚገቡ ሰዎች መሃል እንሆናለን። ሩቅ ያሉትን ለመውደድ፣ ፀጋ የሚያስፈልጋቸውን እናይ ዘንድ ዓይናችን እንዲከፈት እንዲሁም እጆቻችንን በመክፈት ሰዎችን ለመሰብሰብ ድልድይ የምንሰራ እንጂ ሰዎችን የምናስወጣ አጥሮች አይደለንም፡፡ ዓለምን መቀየር የምንፈልግ ከሆነ አስቀድመን ራሳችንን ለመለወጥ የምንፈቅድ መሆን አለብን፡፡ ባልንጀራችንን መውደድ ከሚያስከፍለው ዋጋ አንዱ ስህተት የቱ ጋር እንዳለን ለመቀበል ትሁት ስንሆን ነው። እስቲ ልባችንን እንፈትነው፣ አስፈላጊ ከሆነም ንስሃ እንግባ፣ እግዚአብሔር እንዲረዳንም እንፀልይና “ሒዱና እንደዚሁ አድርጉ” የሚለውን እንተግብረው፡፡

እግዚአብሔር በዓለም ዙሪያ በዘረኝነት ምክንያት ለወደመው ሁሉ እንደ አዲስ የምታደርጉ የእርሱ ምርጥ መፍትሔ ትሆኑ ዘንድ ኃይል ያስታጥቃችሁ፡፡ በመንገድህ የሌሎችን ስቃይ አይተህ እንድትሄድላቸው ቀስ እንድትል ሲያደርግህም ሆነ ሲያስቆምህ መንግስቱ እንደምትመጣ ማስተዋልን፣ ብርታትን፣ ፅናትንና የማያባራ መሰጠትን ይስጥህ፡፡ ለሚገጥሙን ሰዎች ፍቅርንና አክብሮትን ከማሳየት ረገድ ፍፁም የሆነ ባህላዊና ማህበራዊ ለውጦችን መለማመድ መጀመር ይሁንልን፡፡

ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

ዘረኝነትና የእኛ ምላሽ

እንደ ክርስቲያን በዙሪያችን ባለው ዓለም ያለውን የዘረኝነት ውጤትና የእኛን ምላሽ መመልከት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ጊዜውን የጠበቀ እጅግ አስደሳች የአራት ቀናት ዕቅድ የዘረኝነትን ስር እንዲሁም በዚህ ዓለም በእግዚአብሔር የመዋጀትና የተሃድሶ ስራ ውስጥ እንድንጫወት የተጠራንበትን ጉዳይ ይዳስሳል፡፡ ይህ ዕቀድ የተዘጋጀው በዩቨርዥን ነው፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Sidhara Udalagama ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.linkedin.com/in/sidhara-udalagama-b89b32210/?originalSubdomain=au

ተዛማጅ እቅዶች