1
1 ቆሮንቶስ 13:4-5
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፤ በደልን አይቈጥርም።
Compare
Explore 1 ቆሮንቶስ 13:4-5
2
1 ቆሮንቶስ 13:7
ፍቅር ሁልጊዜ ይታገሣል፤ ሁልጊዜ ያምናል፤ ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል።
Explore 1 ቆሮንቶስ 13:7
3
1 ቆሮንቶስ 13:6
ፍቅር ከእውነት ጋራ እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም።
Explore 1 ቆሮንቶስ 13:6
4
1 ቆሮንቶስ 13:13
እንግዲህ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።
Explore 1 ቆሮንቶስ 13:13
5
1 ቆሮንቶስ 13:8
ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ነገር ግን ትንቢት ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ይሻራል።
Explore 1 ቆሮንቶስ 13:8
6
1 ቆሮንቶስ 13:1
በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ።
Explore 1 ቆሮንቶስ 13:1
7
1 ቆሮንቶስ 13:2
የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ ምስጢርን ሁሉና ዕውቀትን ሁሉ ባውቅ፣ ተራራንም ከቦታው የሚነቅል እምነት ቢኖረኝ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
Explore 1 ቆሮንቶስ 13:2
8
1 ቆሮንቶስ 13:3
ያለኝን ሁሉ ለድኾች ብሰጥ፣ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ለእሳት ብዳርግ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።
Explore 1 ቆሮንቶስ 13:3
9
1 ቆሮንቶስ 13:11
ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ ዐስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላ ነበር። ከጐለመስሁ በኋላ ግን የልጅነትን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ።
Explore 1 ቆሮንቶስ 13:11
Home
Bible
Plans
Videos