1
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:5
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
በጸሎት ለመትጋት ሁለታችሁም ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር በመለያየት አንዱ የሌላውን የጋብቻ መብት አይከልክል። በዚህም ምክንያት ራሳችሁን መቈጣጠር አቅቶአችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ።
Compare
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:5
2
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:3-4
ባል ለሚስቱ ማድረግ የሚገባውን የጋብቻ መብትዋን አይከልክላት፤ እንዲሁም ሚስት ለባልዋ ማድረግ የሚገባትን የጋብቻ መብቱን አትከልክለው። ሚስት በሰውነቷ ላይ ሥልጣን የላትም፤ በእርስዋ ሰውነት ላይ ሥልጣን ያለው ባልዋ ነው። እንዲሁም ባል በሰውነቱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ በእርሱ ሰውነት ላይ ሥልጣን ያላት ሚስቱ ነች።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:3-4
3
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:23
እግዚአብሔር በዋጋ ስለ ገዛችሁ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:23
Home
Bible
Plans
Videos