1
1 የጴጥሮስ መልእክት 2:9
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
Compare
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 2:9
2
1 የጴጥሮስ መልእክት 2:24-25
ከኃጢአት ተለይተን በጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል። እናንተ እንደ ጠፉ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 2:24-25
3
1 የጴጥሮስ መልእክት 2:10
እናንተ ቀድሞ የእግዚአብሔር ሕዝብ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ናችሁ፤ ቀድሞ ምሕረት አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረት አግኝታችኋል።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 2:10
4
1 የጴጥሮስ መልእክት 2:2
አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ወተት እንደሚመኙ እናንተም ለመዳን እያደጋችሁ የምትሄዱበትን ንጹሑን መንፈሳዊ ትምህርት ተመኙ።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 2:2
5
1 የጴጥሮስ መልእክት 2:11-12
ወዳጆች ሆይ፥ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች ስለ ሆናችሁ ከነፍስ ጋር ከሚዋጉት ከሥጋ ፍትወቶች እንድትርቁ ዐደራ እላችኋለሁ። ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ቀን አሕዛብ መልካም ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በእነርሱ መካከል ስትኖሩ መልካም ጠባይ ይኑራችሁ።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 2:11-12
6
1 የጴጥሮስ መልእክት 2:5
ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 2:5
7
1 የጴጥሮስ መልእክት 2:1
እንግዲህ ክፋትን ሁሉ፥ ማታለልን ሁሉ፥ ግብዝነትን፥ ቅናትን፥ ማንኛውንም ዐይነት ሐሜት አስወግዱ፤
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 2:1
8
1 የጴጥሮስ መልእክት 2:4
ስለዚህ ሕያው ድንጋይ ወደ ሆነው ወደ ጌታ ኢየሱስ ቅረቡ፤ ይህ ድንጋይ ሰዎች ንቀው የተዉት፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የተመረጠና ክቡር ዋጋ ያለው ነው።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 2:4
9
1 የጴጥሮስ መልእክት 2:16
እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ሆናችሁ በነጻነት ኑሩ እንጂ ነጻነታችሁን የክፋት መሸፈኛ አታድርጉት።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 2:16
10
1 የጴጥሮስ መልእክት 2:15
መልካም በማድረግ የሞኞችን አላዋቂ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 2:15
Home
Bible
Plans
Videos