1
1 የጴጥሮስ መልእክት 1:3-4
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱም የማይጠፋውን፥ የማይበላሸውንና የማያረጀውን ርስት በሰማይ አዘጋጅቶላችኋል።
Compare
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 1:3-4
2
1 የጴጥሮስ መልእክት 1:6-7
ምንም እንኳ የተለያዩ ፈተናዎች ለጥቂት ጊዜ የሚያስቸግሩአችሁ ቢሆኑ በእርሱ ደስ ይበላችሁ። ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 1:6-7
3
1 የጴጥሮስ መልእክት 1:15-16
ነገር ግን የጠራችሁ እግዚአብሔር ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተም በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤ “እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ተብሎ ተጽፎአል።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 1:15-16
4
1 የጴጥሮስ መልእክት 1:14
ታዛዦች ልጆች ሆናችሁ ባለማወቅ ቀድሞ የነበራችሁን ክፉ ምኞት አትከተሉ፤
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 1:14
5
1 የጴጥሮስ መልእክት 1:13
ስለዚህ ልቡናችሁን አንቅታችሁ ለሥራ ተዘጋጁ፤ በመጠን ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ለምታገኙት ጸጋ ሙሉ ተስፋ ይኑራችሁ።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 1:13
6
1 የጴጥሮስ መልእክት 1:24-25
መጽሐፍ እንደሚለው፦ “ሥጋ ለባሽ ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ዱር አበባ ነው፤ ሣሩም ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የጌታ ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።” የተሰበከላችሁም የምሥራች ቃል ይኸው ነው።
Explore 1 የጴጥሮስ መልእክት 1:24-25
Home
Bible
Plans
Videos