1
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ስለዚህ ማንም ሰው የክርስቶስ ወገን ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ፍጥረት አልፎአል፤ በእርሱም ስፍራ አዲስ ፍጥረት ተተክቶአል።
Compare
Explore 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17
2
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21
እኛ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተካፋዮች እንድንሆን እግዚአብሔር ኃጢአት የሌለበትን ክርስቶስን የእኛን ኃጢአት እንዲሸከም አደረገው።
Explore 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21
3
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:7
እኛ የምንኖረውም ጌታን በማመን እንጂ እርሱን በማየት አይደለም።
Explore 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:7
4
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:18-19
ይህም ሁሉ የሆነው እኛን ከራሱ ጋር በክርስቶስ አማካይነት ባስታረቀንና የማስታረቅንም አገልግሎት በሰጠን በእግዚአብሔር ነው። ይህም እግዚአብሔር በክርስቶስ የዓለምን ሰዎች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ ማለት ነው፤ በደላቸውንም አልቈጠረባቸውም፤ ለእኛም ሰውን ከጌታ ጋር የምናስታርቅበትን ቃል ሰጠን።
Explore 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:18-19
5
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:20
እግዚአብሔር ሰዎችን በእኛ አማካይነት ስለሚጠራ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ ስለዚህ “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!” ብለን በክርስቶስ ስም እንለምናችኋለን።
Explore 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:20
6
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15-16
በሕይወት ያሉት ሁሉ ለእነርሱ ለሞተውና ከሞትም ለተነሣው እንዲኖሩ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ ለራሳቸው ሲሉ እንዳይኖሩ ክርስቶስ ለሁሉም ሞተ። ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ማንንም ሰው በሥጋዊ አመለካከት አንመለከትም፤ ከዚህ በፊት ክርስቶስንም የተመለከትነው እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋዊ አመለካከት ከሆነ ለወደፊቱ ግን ይህን አናደርግም።
Explore 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15-16
7
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:14
አንድ ጊዜ ክርስቶስ ለሁሉም መሞቱንና ሁሉም የእርሱ ሞት ተካፋዮች መሆናቸውን ስለ ተረዳን የክርስቶስ ፍቅር ለሥራ ያስገድደናል።
Explore 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:14
Home
Bible
Plans
Videos