1
ኦሪት ዘዳግም 8:18
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ባለጸጋ እንድትሆን ኀይልና ብርታት የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ እርሱ ይህን የሚያደርግበት ምክንያት ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።
Compare
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:18
2
ኦሪት ዘዳግም 8:3
በራብ እንድትሠቃይ አደረገህ፤ ቀጥሎም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ የማታውቁትን መና አበላህ፤ ይህንንም ማድረጉ ሰው ሕይወቱ ተጠብቆለት መኖር የሚችለው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አለመሆኑን ሊያስተምርህ ነው።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:3
3
ኦሪት ዘዳግም 8:2
አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዞች ስለ መጠበቅህ በልብህ ያለውን ሐሳብ ያውቅ ዘንድ አንተን ለመፈተን በዚህ በረሓ አርባ ዓመት ሙሉ በመከራ ውስጥ በማሳለፍ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:2
4
ኦሪት ዘዳግም 8:17
ስለዚህም ‘ባለጸጋ የሆንኩት በራሴ ኀይልና ብርታት ነው’ ብለህ ከቶ አታስብ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:17
5
ኦሪት ዘዳግም 8:11
“እግዚአብሔር አምላክህን በመርሳት፥ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች፥ ደንቦችና ሥርዓቶች እንዳታፈርስ ተጠንቀቅ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:11
6
ኦሪት ዘዳግም 8:5
አባት ልጆቹን እንደሚገሥጽ አምላክህ እግዚአብሔርም አንተን የሚገሥጽህ መሆኑን አስተውል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:5
7
ኦሪት ዘዳግም 8:10
በልተህ ትጠግባለህ፤ ይህችን ለም ምድር የሰጠህን እግዚአብሔር አምላክህንም ታመሰግናለህ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:10
8
ኦሪት ዘዳግም 8:6
እርሱን በመፍራትና የእርሱንም መንገድ በመከተል፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቅ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:6
9
ኦሪት ዘዳግም 8:16
ሊያዋርድህና ሊፈትንህ፥ በመጨረሻም መልካም ነገር ሊያደርግልህ የቀድሞ አባቶችህ ተመግበው የማያውቁትን መና በምድረ በዳ ሰጠህ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:16
10
ኦሪት ዘዳግም 8:12-14
በልተህ በምትጠግብበትና ጥሩ ቤቶች ሠርተህ በምትኖርበት ጊዜ፥ የከብቶችህና የበጎችህ መንጋ፥ ብርህና ወርቅህ እንዲሁም ሌላው ሀብትህ ሁሉ በበዛልህ ጊዜ፥ ልብህ እንዳይታበይና በባርነት ከኖርክባት ከግብጽ ምድር ያወጣህን አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:12-14
11
ኦሪት ዘዳግም 8:7-9
እነሆ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካሚቱ ለምለም ምድር ሊያስገባህ አምጥቶሃል፤ ያቺም ምድር ከሸለቆዎችና ከኮረብቶች የሚመነጩ ወንዞችና ጅረቶች፥ ፈሳሾች ምንጮችም ይገኙበታል፤ ስንዴና ገብስ፥ ወይንና በለስ፥ ሮማንና የወይራ ፍሬ፥ ማርም የሞላባት ናት፤ ምድሪቱ ሳይጓደልብህ እንጀራ የምትበላባትና ምንም ነገር የማታጣባት ናት፤ ከድንጋዮችዋ ብረት፥ ከኮረብቶችዋም መዳብ ይገኛል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:7-9
12
ኦሪት ዘዳግም 8:1
“በሕይወት መኖር እንድትችሉ፥ ቊጥራችሁ እንዲበዛ፥ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውን ምድር ለመውረስ እንድትበቁ፥ ዛሬ እኔ የሰጠኋችሁን ትእዛዝ ሁሉ በታማኝነት ጠብቁ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:1
13
ኦሪት ዘዳግም 8:4
በእነዚህም አርባ ዓመቶች ውስጥ ልብስህ አላለቀም፤ ከጒዞም የተነሣ እግርህ አላበጠም።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:4
14
ኦሪት ዘዳግም 8:15
መርዘኛ እባብና ጊንጥ በሞላበት፥ አስፈሪ በሆነው በዚያ ሰፊ በረሓ መርቶሃል፤ ምንም ውሃ በማይገኝበት ደረቅ በረሓ ከጽኑ አለት ውሃን አፈለቀልህ፤
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:15
Home
Bible
Plans
Videos